ዘፍጥረት 14:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሖር ሰዎችንም በተራራማው አገር በኤዶም፥ በበረሓ አጠገብ እስካለው እስከ ኤልፋራን ባለው ስፍራ ድል ነሡአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሖሪ ሰዎችንም በተራራማው አገር በሴይር በረሓማ አጠገብ እስካለው እስከ ኤልፋራን ድረስ ድል አደረጓቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሖር ሰዎችንም በሴይር ተራራቸው በበረሀ አጠገብ እስካለች እስከ ኤል ፋራን ድረስ መቱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሴይር ተራራዎች ያሉ የኬሬዎስ ሰዎችንም በበረሃ አጠገብ እስከ አለችው እስከ ፋራን ዛፍ ድረስ መቱአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሖር ሰዎችንም በሴይር ተራራቸው በበረሀ አጠገብ እስካለች እስከ ኤል ፋራን ድረስ መቱ። |
እነርሱም ከምድያም ተነሥተው ወደ ፋራን ሄዱ፤ በዚያም ጥቂቶች ሰዎች ከእነርሱ ጋር ተቀላቀሉ፤ ከዚህ በኋላ ወደ ግብጽ ተጒዘው ወደ ንጉሡ ቀረቡ፤ ንጉሡም ለሀዳድ መሬትና አንድ መኖሪያ ቤት ሰጥቶ ምግብ ፈቀደለት፤
እግዚአብሔር በቅድስናው ከቴማን አገርና፥ ከፋራን ተራራ እንደገና ይመጣል፤ መለኮታዊ ክብሩ ሰማያትን ሸፍኖአል፤ ምስጋናውም ምድርን ሞልቶአል።
ሖራውያንም በኤዶም ይኖሩ ነበር፤ ነገር ግን የዔሳው ዘሮች ሖራውያንን ነቃቅለው በማባረር በእነርሱ ቦታ ሰፍረውበት ነበር፤ ይኸውም እስራኤላውያን ዘግየት ብለው እግዚአብሔር በሰጣቸው ምድር ላይ እንዳደረጉት ዐይነት መሆኑ ነው።]
እግዚአብሔር ኮረብታማ በሆነችው በኤዶም ለሚኖሩት ለዔሳው ዘሮችም እንደዚሁ አድርጎላቸው ነበር፤ ይኸውም ቀድሞ የኖሩባትን ሖራውያንን ደምስሶ እስከ አሁን የሚኖሩባትን ምድራቸውን ኤዶማውያን ወርሰው እንዲሰፍሩባት አድርጎአል።