ዘፍጥረት 10:29 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኦፊር፥ ሐዊላና ዮባብ ናቸው፤ እነዚህ ሁሉ የዮቅጣን ዘሮች ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የኦፊር፣ የኤውላጥ፣ የዮባብ አባት ነበረ፤ እነዚህ ሁሉ የዮቅጣን ልጆች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኦፊር፥ ሐዊላና ዮባብ ናቸው፤ እነዚህ ሁሉ የዮቅጣን ዘሮች ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አፌርንም፥ ኤውላጥንም፥ ዮባብንም ወለደ፤ እነዚህ ሁሉ የዮቅጣን ልጆች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳባንም፥ ኦፊርንም፥ ኤውላጥንም፥ ዩባብንም ወለደ፤ እነዚህ ሁሉ የዩቅጣን ልጆች ናቸው። |
የእስማኤል ዘሮች ከግብጽ በስተምሥራቅ ወደ አሦር በምትወስደው መንገድ በሐዊላና በሹር መካከል ይኖሩ ነበር፤ የኖሩትም ከሌሎቹ የአብርሃም ዘሮች ጋር በጥላቻ ተራርቀው ነበር።
ንጉሥ ኢዮሣፍጥ ውቅያኖስን አቋርጠው ከኦፊር ወርቅ የሚያመጡለትን የተርሴስ ዐይነት መርከቦች አሠርቶ ነበር፤ ነገር ግን መርከቦቹ በኤጽዮንጋብር ወደብ ላይ ስለ ተሰበሩ መጓዝ አልቻሉም።
እነርሱም በመርከብ ተጒዘው ወደ ኦፊር ምድር ከሄዱ በኋላ ወደ ንጉሡ ወደ ሰሎሞን ሲመለሱ ከዐሥራ አራት ሺህ ኪሎ ግራም በላይ የሚመዝን ወርቅ ይዘውለት መጡ።
በኢየሩሳሌም ይኖሩ የነበሩት ካህናት የሚከተሉት ናቸው፦ ይዳዕያ፥ ይሆያሪብና ያኪን፤ በቤተ መቅደስ ዋና ባለሥልጣን የሆነው የሒልቂያ ልጅ ዐዛርያስ፤ የእርሱም የቀድሞ አባቶች መሹላም፥ ጻዶቅ፥ መራዮትና አሒጡብ ናቸው። የይሮሐም ልጅ ዐዳያ፤ የእርሱም የቀድሞ አባቶች ፓሽሑር ማልኪያ ናቸው። የዐዲኤል ልጅ ማዕሳይ፤ የእርሱም የቀድሞ አባቶች ያሕዜራ፥ መሹላም፥ መሺሌሚትና ኢሜር ናቸው።
የቤተሰብ አለቆች የነበሩት ካህናት በድምሩ አንድ ሺህ ሰባት መቶ ሥልሳ ነበሩ፤ እነዚህ ሁሉ በቤተ መቅደስ ውስጥ ለሚከናወነው ሥራ በቂ ችሎታ ያላቸው ነበሩ።
በቤተ መንግሥትህ ከሚገኙት ወይዛዝርት መካከል፥ የነገሥታት ሴቶች ልጆች ይገኛሉ፤ ንግሥቲቱም በንጹሕ ወርቅ ያሸበረቀ ጌጠኛ ልብስ ተጐናጽፋ ከዙፋንህ በስተቀኝ ቆማለች።