ዘፍጥረት 1:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር “ብርሃን ይሁን” አለ፤ ብርሃንም ሆነ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም “ብርሃን ይሁን” አለ፤ ብርሃንም ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔርም፦ “ብርሃን ይሁን” ኣለ፤ ብርሃንም ሆነ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም፥ “ብርሃን ይሁን” አለ፤ ብርሃንም ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም፤ ብርሃን ይሁን ኣለ፤ ብርሃንም ሆነ። |
“ብርሃን በጨለማ ውስጥ ይብራ!” ብሎ የተናገረ እግዚአብሔር በክርስቶስ መልክ የሚያበራውን የእግዚአብሔርን ክብር የማወቅ ብርሃን እንዲሰጠን ብርሃኑን በልባችን ውስጥ እንዲበራ አደረገ።
እርሱ ብቻ የማይሞት ነው፤ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፤ እርሱን ከቶ ማንም አላየውም፤ ማንም ሊያየውም አይችልም፤ ክብርና ዘለዓለማዊ ኀይል ለእርሱ ይሁን፤ አሜን።
ይሁን እንጂ በክርስቶስና በእናንተ ሕይወት ዘንድ እውነት ሆኖ የታየውን አዲስ ትእዛዝ እጽፍላችኋለሁ፤ ጨለማው ተወግዶ እውነተኛው ብርሃን አሁንም እያበራ ነው።