ስለዚህ ጳውሎስና በርናባስ የጌታን ነገር በድፍረት እየተናገሩ እዚያ ብዙ ጊዜ ቈዩ፤ ጌታም ተአምራትና ድንቅ ነገሮች በእነርሱ እጅ እንዲደረጉ ሥልጣን በመስጠት፥ የእርሱ የጸጋ ቃል እውነተኛ መሆኑን ያረጋግጥ ነበር።
ገላትያ 3:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር መንፈሱን የሚሰጣችሁና በእናንተ ዘንድ ተአምራትን የሚያደርገው ሕግን በመፈጸማችሁ ነውን? ወይስ የምሥራቹን ቃል ሰምታችሁ በማመናችሁ ነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር መንፈሱን የሚሰጣችሁ፣ በእናንተም ዘንድ ታምራትን የሚሠራው ሕግን ስለ ጠበቃችሁ ነው ወይስ የሰማችሁትን ስላመናችሁ? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲህ መንፈስን የሚሰጣችሁ በእናንተም ድንቅን የሚሠራ፥ በሕግ ሥራ ነውን? ወይስ በእምነት በመስማታችሁ ነው? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱ መንፈስ ቅዱስን የሚሰጣችሁ፥ ኀይልንም የሚያደርግላችሁ የኦሪትን ሥራ በመሥራት ነውን? ወይስ ሃይማኖትን በመስማት ነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ መንፈስን የሚሰጣችሁ በእናንተም ዘንድ ተአምራት የሚያደርግ፥ በሕግ ሥራ ነውን ወይስ ከእምነት ጋር በሆነ መስማት ነው? |
ስለዚህ ጳውሎስና በርናባስ የጌታን ነገር በድፍረት እየተናገሩ እዚያ ብዙ ጊዜ ቈዩ፤ ጌታም ተአምራትና ድንቅ ነገሮች በእነርሱ እጅ እንዲደረጉ ሥልጣን በመስጠት፥ የእርሱ የጸጋ ቃል እውነተኛ መሆኑን ያረጋግጥ ነበር።
እንዲሁም በታላላቅ ተአምራትና በድንቅ ሥራዎች፥ በመንፈስ ቅዱስም ኀይል ከኢየሩሳሌምና ከአካባቢዋ ጀምሮ እስከ እልዋሪቆን ድረስ የክርስቶስን ወንጌል አስተምሬአለሁ።
እንዲሁም ለአንዱ ተአምራትን የማድረግ ኀይል ይሰጠዋል፤ ለሌላው የትንቢትን ቃል የመናገር ችሎታ ይሰጠዋል፤ ለሌላው ደግሞ ስጦታዎች ከመንፈስ ቅዱስ መሆናቸውን ወይም ከርኩሳን መናፍስት መሆናቸውን ለይቶ የማወቅ ችሎታን ይሰጠዋል፤ እንዲሁም ለአንዱ በተለያዩ ቋንቋዎች የመናገር ችሎታን ይሰጠዋል፤ ለሌላው ደግሞ በተለያዩ ቋንቋዎች የተነገረውን የመተርጐም ችሎታን ይሰጠዋል፤
እኔ እውነተኛ ሐዋርያ መሆኔን የሚያስረዱት ነገሮች እኔ በመካከላችሁ ሳለሁ በትዕግሥት የፈጸምኳቸው ሥራዎች ናቸው፤ እነዚህም ምልክቶችና ድንቅ ነገሮች ተአምራትም ናቸው።
እናንተ በእኔ ዐድሮ የሚናገረው ክርስቶስ መሆኑን ለማረጋገጥ ትፈልጋላችሁ፤ በእናንተ ዘንድ የሚታየውም የእርሱ ኀይል ነው እንጂ ድካሙ አይደለም።
ማወቅ የምፈልገው ይህን ብቻ ነው፤ ለመሆኑ እናንተ መንፈስ ቅዱስን የተቀበላችሁት ሕግን በመፈጸም ነውን? ወይስ የምሥራቹን ቃል ሰምታችሁ በማመን ነው?