እነርሱም ወደ ሕግህ እንዲመለሱ አስጠነቀቅኻቸው፤ በትዕቢታቸው ግን ትእዛዞችህን ናቁ፤ ቢፈጽሙአቸው ሕይወት በሚሰጡት ሕጎችህ ላይ ኃጢአት ሠሩ። በልበ ደንዳናነት ፊታቸውን አዞሩ፤ በእልኸኛነታቸውም እምቢተኞች ሆኑ።
ገላትያ 3:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕግ በእምነት ላይ የተመሠረተ አይደለም፤ እንዲያውም “ሰው በሕግ ሊኖር የሚችለው የሕግ ትእዛዞችን ሁሉ ሲፈጽም ነው” ተብሎ ተጽፎአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕግ በእምነት ላይ የተመሠረተ አይደለም፤ ነገር ግን “እነዚህን የሚፈጽም ሰው በእነርሱ ሕያው ይሆናል” ተብሏል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕግ ከእምነት አይደለም፤ ነገር ግን “የሚፈጽማቸው በእነርሱ ይኖራል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኦሪትስ ሠርቶ የፈጸመ ይኖርበታል እንጂ በእምነት የሚያጸድቅ አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕግም ከእምነት አይደለም ነገር ግን፦ የሚያደርገው ይኖርበታል ተብሎአል። |
እነርሱም ወደ ሕግህ እንዲመለሱ አስጠነቀቅኻቸው፤ በትዕቢታቸው ግን ትእዛዞችህን ናቁ፤ ቢፈጽሙአቸው ሕይወት በሚሰጡት ሕጎችህ ላይ ኃጢአት ሠሩ። በልበ ደንዳናነት ፊታቸውን አዞሩ፤ በእልኸኛነታቸውም እምቢተኞች ሆኑ።
ነገር ግን እስራኤላውያን በበረሓ ሳሉ እንኳ በእኔ ላይ ዐመፁ፤ ለሚታዘዝለት ሁሉ ሕይወትን የሚያስገኝለትን ሕጌንና ሥርዓቴን ጣሱ፤ ፈጽመውም ሰንበትን አረከሱ፤ በዚያም በበረሓ ቊጣዬን በእነርሱ ላይ በመግለጥ ላጠፋቸው አስቤ ነበር፤
ኢየሱስም “ስለ መልካም ነገር ለምን ትጠይቀኛለህ? መልካም የሆነ አንድ አምላክ ብቻ ነው፤ ወደ ሕይወት ለመግባት ብትፈልግ ግን ትእዛዞችን ፈጽም” አለው።
ስለዚህ ተስፋው የተመሠረተው በእምነት ላይ ነበር፤ ይህም ተስፋ ለአብርሃም ዘሮች ሁሉ ከእግዚአብሔር በጸጋ የተሰጠ መሆኑ በዚህ ተረጋግጦአል። ይህም ሕግን ለሚከተሉት ሰዎች ብቻ ሳይሆን እንደ አብርሃም ላመኑ ሁሉ ነው፤ በዚህም መሠረት አብርሃም የሁላችንም አባት ነውና።