Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ነህምያ 9:29 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 እነርሱም ወደ ሕግህ እንዲመለሱ አስጠነቀቅኻቸው፤ በትዕቢታቸው ግን ትእዛዞችህን ናቁ፤ ቢፈጽሙአቸው ሕይወት በሚሰጡት ሕጎችህ ላይ ኃጢአት ሠሩ። በልበ ደንዳናነት ፊታቸውን አዞሩ፤ በእልኸኛነታቸውም እምቢተኞች ሆኑ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 “ወደ ሕግህ እንዲመለሱ አስጠነቀቅሃቸው፤ እነርሱ ግን እብሪተኞች ሆኑ። ትእዛዞችህንም አልፈጸሙም፤ ‘አንድ ሰው ቢፈጽማቸው በሕይወት የሚኖርባቸውን’ ሥርዐቶችህን ተላለፉ። እንቢተኞች ሆነው ጀርባቸውን አዞሩብህ፤ ዐንገታቸውን አደነደኑ፤ መስማትም አልፈለጉም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 ወደ ሕግህም ትመልሳቸው ዘንድ አስመሰከርህባቸው፥ ነገር ግን ታበዩ፥ ትእዛዝህንም አልሰሙም፥ ሰውም ባደረገው ጊዜ በሕይወት የሚኖርበትን ፍርድህን ተላለፉ፥ ትከሻቸውንም ሰጡ፥ አንገታቸውን አደነደኑ፥ አልሰሙምም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 ወደ ሕግ​ህም ትመ​ል​ሳ​ቸው ዘንድ አስ​መ​ሰ​ከ​ር​ህ​ባ​ቸው፤ ነገር ግን አል​ሰ​ሙ​ህም፤ ሰውም ባደ​ረ​ገው ጊዜ በሕ​ይ​ወት የሚ​ኖ​ር​በ​ትን ትእ​ዛ​ዝ​ህ​ንና ፍር​ድ​ህን ተላ​ለፉ፤ ጀር​ባ​ቸ​ውን ሰጡ፤ አን​ገ​ታ​ቸ​ው​ንም አደ​ነ​ደኑ፤ አል​ሰ​ሙ​ምም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 ወደ ሕግህም ትመልሳቸው ዘንድ አስመሰከርህባቸው፥ ነገር ግን ታበዩ፥ ትእዛዝህንም አልሰሙም፥ ሰውም ባደረገው ጊዜ በሕይወት የሚኖርበትን ፍርድህን ተላለፉ፥ ትከሻቸውንም ሰጡ፥ አንገታቸውን አደነደኑ፥ አልሰሙምም።

Ver Capítulo Copiar




ነህምያ 9:29
34 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔርም እስራኤልንና ይሁዳን የሚያስጠነቅቁ መልእክተኞችንና ነቢያትን በመላክ “ከክፉ መንገዳችሁ ሁሉ ተመለሱ፤ አገልጋዮቼ በሆኑት ነቢያትና ባለ ራእዮች አማካይነት ለቀድሞ አባቶቻችሁና ለእናንተም በሰጠሁት ሕጎችና ትእዛዞች የተጻፈውን ሥርዓቴን ጠብቁ” ብሎ ነግሮአቸው ነበር።


እነርሱ ግን መታዘዝ አልፈለጉም፤ በአምላካቸው በእግዚአብሔር እንዳልታመኑ እንደ ቀድሞ አባቶቻቸው እልኸኞች ሆኑ፤


እግዚአብሔር ወደ እርሱ እንዲመለሱ አጥብቀው ያሳስቡአቸው ዘንድ ነቢያትን ላከ፤ መሰከሩባቸውም፤ እነርሱ ግን አላዳመጡም፤


እግዚአብሔር ምናሴንና ሕዝቡን በብርቱ ያስጠነቀቃቸው ቢሆንም እንኳ እነርሱ መስማትን እምቢ አሉ፤


የቀድሞ አባቶቻቸው አምላክ እግዚአብሔር ለሕዝቡና ለቤተ መቅደሱ ስላዘነ ያስጠነቅቁአቸው ዘንድ ነቢያትን መላልሶ መላክን ቀጠለ።


በእነዚያም ቀኖች በይሁዳ በሰንበት ቀን ወይን የሚጨምቁ፥ እህልን፥ ወይን ጠጅን፥ የወይን ዘለላን፥ በለስን፥ ሌሎችንም ነገሮች ሁሉ በአህያ የሚጭኑ መሆናቸውን አየሁ፤ እነዚህንም ሁሉ በሰንበት ቀን ወደ ኢየሩሳሌም አምጥተው እንዳይሸጡ አስጠነቀቅኋቸው።


በግብጽ ንጉሥ ላይ በባለሥልጣኖቹና በምድሩ በሚኖሩትም ሕዝብ ሁሉ ላይ ድንቅ ተአምራትን ገልጠህ አሳየህ። ይህንንም ያደረግኸው የቀድሞ አባቶቻችን እንዴት እንደሚጨቈኑ በማየትህ ነው፤ ይህንንም በማድረግህ እስከ ዛሬ ድረስ ዝናህ የገነነ ሆኖአል።


ነገር ግን የቀድሞ አባቶቻችን ትዕቢተኞችና እልኸኞች ሆኑ፤ ትእዛዞችህንም አልጠበቁም፤


“ነገር ግን እነርሱ በአንተ ላይ ዐምፀው ለቃልህ አንታዘዝም አሉ፤ ሕግህንም ላለመስማት ፊታቸውን መለሱ፤ በማስጠንቀቅ ወደ አንተ እንዲመለሱ ያስተማሩአቸውን ነቢያትህን ገደሉ፤ በየጊዜውም በአንተ ላይ ክፉ የስድብ ቃል ተናገሩ፤


አንተም ለብዙ ዓመቶች ታገሥካቸው፤ ያስተምሩአቸውም ዘንድ ነቢያትን በመንፈስህ አስነሣህላቸው፤ ነገር ግን እነርሱ አላዳመጡም፤ ስለዚህም ለጐረቤት ሕዝቦች ድል እንዲነሡአቸው አሳልፈህ ሰጠሃቸው።


ስለዚህ ሙሴና አሮን ወደ ንጉሡ ሄደው እንዲህ አሉት፤ “የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ለእኔ መታዘዝን እምቢ የምትለው እስከ መቼ ነው? አሁንም ያገለግለኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ፤


የቀድሞ አባቶቻችሁ ቃሌን አላዳመጡም፤ ትእዛዜንም አልፈጸሙም፤ ይልቁንም እልኸኞች በመሆን ለእኔ መታዘዝንና ከእኔ መማርን እምቢ አሉ።


“የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነርሱ እልኸኞች ሆነው ለቃሌ ስላልታዘዙ በዚህች ከተማና በዙሪያዋ በሚገኙ ስፍራዎች ሁሉ ይመጣል ብዬ ያስታወቅኹትን መቅሠፍት ሁሉ አመጣባቸዋለሁ።”


“እናንተ ከስደት የተረፋችሁ የይሁዳ ሕዝብ ሆይ! ወደ እግዚአብሔር በላካችሁኝ ጊዜ እርሱ የሚያዘውን ሁሉ ንገረንና እንፈጽማለን ብላችሁ የማትፈጽሙትን ቃል በመግባታችሁ አደገኛ ስህተት ሠርታችኋል፤ አሁንም እግዚአብሔር ወደ ግብጽ አትሂዱ ብሎ ስለ ከለከለ እኔም ዛሬ ይህ ትእዛዝ እርግጠኛ መሆኑን በመግለጥ አስጠነቅቃችኋለሁ።


ከዚያ በኋላ የሆሻያ ልጅ ዐዛርያስ፥ የቃሬሐ ልጅ ዮሐናንና ትዕቢተኞች የሆኑ ሌሎችም ሰዎች ሁሉ እንዲህ አሉ፦ “ውሸትህን ነው፤ አምላካችን እግዚአብሔር እኛ ወደ ግብጽ ሄደን እዚያ እንዳንኖር ትነግረን ዘንድ አላከህም፤


ነገር ግን እስከ ዛሬ ድረስ ራሳችሁን ዝቅ በማድረግ ትሑታን ሆናችሁ አልተገኛችሁም፤ ለእኔ ክብር አልሰጣችሁኝም፤ ለቀድሞ አባቶቻችሁና ለእናንተ በሰጠሁትም ሕግና ደንብ ጸንታችሁ መኖር አልፈለጋችሁም።


ነገር ግን ያዳመጠኝም ሆነ ለትእዛዜ ትኲረት የሰጠ ሰው አልነበረም፤ ይልቁንም ከቀድሞ አባቶቻችሁ ብሳችሁ እልኸኞችና ዐመፀኞች ሆናችሁ።”


ለሚታዘዘው ሁሉ በሕይወት መኖር የሚችልበትን ሕጌን ሰጠኋቸው፤ ሥርዓቴንም አስተማርኳቸው፤


ነገር ግን ትዕቢተኛ፥ እልኸኛና ጨካኝ ሆኖ በተገኘ ጊዜ ክብሩንና ማዕርጉን ተገፎ ከዙፋኑ ወረደ፤


በነቢያቴ አማካይነት እንደማጠፋቸው በቃሌም አማካይነት እንደምገድላቸው አስጠነቀቅኋቸው፤ ስለዚህ ፍርዴ እንደ ንጋት ብርሃን ያንጸባርቃል።


እኔ የምሰጣችሁን ኅጎቼንና ሥርዓቴን ጠብቁ፤ ይህን በማድረግ ማናቸውም ሰው ሕይወቱን ያድናል፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።’ ”


ኢየሱስም “ስለ መልካም ነገር ለምን ትጠይቀኛለህ? መልካም የሆነ አንድ አምላክ ብቻ ነው፤ ወደ ሕይወት ለመግባት ብትፈልግ ግን ትእዛዞችን ፈጽም” አለው።


ኢየሱስም “በትክክል መልሰሃል፤ እንግዲህ አንተም ይህን አድርግ! የዘለዓለም ሕይወትንም ታገኛለህ” አለው።


ሕግን በመከተል ስለሚገኘው ጽድቅ ሙሴ የጻፈው “ሕግን የሚፈጽም ሁሉ በሕይወት ይኖራል” የሚል ነው።


ሕግ በእምነት ላይ የተመሠረተ አይደለም፤ እንዲያውም “ሰው በሕግ ሊኖር የሚችለው የሕግ ትእዛዞችን ሁሉ ሲፈጽም ነው” ተብሎ ተጽፎአል።


ብዙ ከባድ ችግሮች ሲደርሱባቸው ይህ በልጆቻቸው የማይረሳ መዝሙር ሲዘመር ምስክር ይሆንባቸዋል። በመሐላ ቃል ወደገባሁላቸው ምድር ከማስገባቴ በፊት አሁን እንኳ ምን ዐይነት ዝንባሌ እንዳላቸው ዐውቃለሁ።”


የእስራኤል ሕዝብ ምን ያኽል ዐመፀኞችና አንገተ ደንዳኖች እንደ ሆኑ ዐውቃለሁ፤ በእኔ ሕይወት ዘመን ከእነርሱ ጋር ሳለሁ እንኳ በእግዚአብሔር ላይ እንዳመፁ ናቸው፤ ከሞትሁ በኋላማ ከዚህ ይበልጥ ያምፃሉ፤


ይህን ብታደርጉ ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ በምትወርስዋት ምድር ረጅም ጊዜ እንደማትኖሩባትና በፍጹም እንደምትደመሰሱ እኔ ዛሬ ሰማይንና ምድርን ምስክር አድርጌ እነግራችኋለሁ።


እኔ አምላካችሁ እግዚአብሔር እንደ ሆንኩና አሁን ምድራቸውን የወረሳችኋቸውን የአሞራውያንን ባዕዳን አማልክት እንዳታመልኩ ነግሬአችሁ ነበር፤ እናንተ ግን አልሰማችሁኝም።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos