የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር የቤተ መቅደሱን፥ የንጉሡንና የእርሱ ባለሟሎች የሆኑትን ባለሥልጣኖች ግምጃ ቤት በሙሉ ዘርፎ ወደ ባቢሎን ወሰደ፤
ዕዝራ 5:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ናቡከደነፆር በዚሁ በኢየሩሳሌም ተሠርቶ ከነበረው ከቀድሞው ቤተ መቅደስ ማርኮ የወሰዳቸውንና በባቢሎን ማምለኪያ ስፍራው ውስጥ ያኖራቸውን ከወርቅና ከብር የተሠሩ ንዋያተ ቅድሳትም ሁሉ ቂሮስ መልሶ አስረክቦናል፤ ንዋያተ ቅድሳቱንም ያስረከበን የይሁዳ ገዢ አድርጎ በሾመው ሼሽባጻር ተብሎ በሚጠራው ሰው አማካይነት ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ናቡከደነፆር ከኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ አውጥቶ ባቢሎን በሚገኘው ቤተ መቅደስ ውስጥ ያኖራቸውን የእግዚአብሔርን ቤት የወርቅና የብር ዕቃዎች ከባቢሎን ቤተ መቅደስ አስመጣ። ከዚያም ንጉሥ ቂሮስ፣ አገረ ገዥ አድርጎ ለሾመውና ሰሳብሳር ተብሎ ለሚጠራው ሰው ሰጠው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ናቡከደነፆር በኢየሩሳሌም ከነበረው መቅደስ የወሰደውን፥ ወደ ባቢሎንም መቅደስ ያመጣውን የእግዚአብሔርን ቤት የወርቅንና የብርን ዕቃዎች ንጉሡ ቂሮስ ከባቢሎን መቅደስ አውጥቶ ሼሽባጻር ለተባለው፥ ገዢ ላደረገው ሰጠው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ናቡከደነፆርም በኢየሩሳሌም ከነበረው መቅደስ የወሰደውን፥ ወደ ባቢሎንም መቅደስ ያፈለሰውን የእግዚአብሔርን ቤት የወርቁንና የብሩን ዕቃ ንጉሡ ቂሮስ ከባቢሎን መቅደስ አውጥቶ ለቤተ መዛግብቱ ሹም ለሲሳብሳር ሰጠውና፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ናቡከደነፆርም በኢየሩሳሌም ከነበረው መቅደስ የወሰደውን፥ ወደ ባቢሎንም መቅደስ ያፈለሰውን የእግዚአብሔርን ቤት የወርቅንና የብርን ዕቃ ንጉሡ ቂሮስ ከባቢሎን መቅደስ አውጥቶ ሰሳብሳር ለተባለው ለሹሙ ሰጠውና፦ |
የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር የቤተ መቅደሱን፥ የንጉሡንና የእርሱ ባለሟሎች የሆኑትን ባለሥልጣኖች ግምጃ ቤት በሙሉ ዘርፎ ወደ ባቢሎን ወሰደ፤
ይኸው አገረ ገዢው ሼሽባጻር እነዚህን ንዋያተ ቅድሳት መልሶ በማምጣት በኢየሩሳሌም ከነበረው ቤተ መቅደስ ውስጥ ያኖር ዘንድ፥ እንዲሁም ቤተ መቅደሱ ቀድሞ በነበረበት ስፍራ ላይ ተመልሶ እንዲሠራ ያደርግ ዘንድ፥ ንጉሠ ነገሥቱ ቂሮስ አዞታል።
ስለዚህም ሼሽባጻር መጥቶ መሠረቱን ጣለ፤ ከዚያም በኋላ የሕንጻው ሥራ እንዲቀጥል ተደርጎ፥ ይኸው እስከ አሁን በመሠራት ላይ ነው፤ ነገር ግን የቤተ መቅደሱ ሕንጻ ገና አልተፈጸመም።’
እንዲሁም ከዚህ በፊት ንጉሥ ናቡከደነፆር በኢየሩሳሌም ከነበረው ቤተ መቅደስ ማርኮ ያወጣቸው ከወርቅና ከብር የተሠሩትም ንዋያተ ቅድሳት ወደዚያው ተመልሰው በኢየሩሳሌም በሚሠራው ቤተ መቅደስ በተገቢ ቦታቸው ይቀመጡ።”
ዕዝራ እንዲህ ሲል እግዚአብሔርን አመሰገነ፦ “የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን! በኢየሩሳሌም ለሚሠራው ለእግዚአብሔር ቤት ንጉሠ ነገሥቱ ክብር ለመስጠት እንዲፈቅድ ያደረገው እርሱ ነው፤
የክብር ዘቡ አዛዥ ጐድጓዳ ሳሕኖችን፥ የዕጣን ማጠኛዎችን፥ ጐድጓዳ ወጭቶችን፥ ድስቶችን፥ መቅረዞችን፥ ጭልፋዎችን፥ የመጠጥ መሥዋዕት ማቅረቢያዎችን፥ በወርቅና በብር የተሠሩ ዕቃዎችን ሁሉ ወሰደ።
ዳርዮስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት፥ ስድስተኛው ወር በገባ በመጀመሪያው ቀን፥ እግዚአብሔር በነቢዩ አማካይነት በሐጌ ተናገረ የተናገረውም የይሁዳ ገዢ ለነበረው ለሰላትያል ልጅ ለዘሩባቤልና ሊቀ ካህናት ለነበረው ለኢዮሴዴቅ ልጅ ለኢያሱ ነው።
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር የይሁዳ ገዢ የሆነውን የሰላትያልን ልጅ ዘሩባቤልን፥ ሊቀ ካህናቱን የኢዮሴዴቅን ልጅ ኢያሱንና ተርፈው ከስደት የተመለሱትን ሰዎች ሁሉ መንፈስ አነሣሣ፤ እነርሱም የአምላካቸውን የሠራዊትን ጌታ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ መሥራት ጀመሩ።
ጌታ ይሁዳ ገዢ ለሆነው ለሰላትያል ልጅ ለዘሩባቤል፥ ሊቀ ካህናት ለሆነው ለኢዮሴዴቅ ልጅ ለኢያሱና ተርፎ ከስደት ለተመለሰው ሕዝብ እንዲህ ብለህ ተናገር አለው።