Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዕዝራ 5:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ይኸው አገረ ገዢው ሼሽባጻር እነዚህን ንዋያተ ቅድሳት መልሶ በማምጣት በኢየሩሳሌም ከነበረው ቤተ መቅደስ ውስጥ ያኖር ዘንድ፥ እንዲሁም ቤተ መቅደሱ ቀድሞ በነበረበት ስፍራ ላይ ተመልሶ እንዲሠራ ያደርግ ዘንድ፥ ንጉሠ ነገሥቱ ቂሮስ አዞታል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ቀጥሎም፣ ‘እነዚህን ዕቃዎች ይዘህ ሂድና በኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ውስጥ አኑራቸው፤ የእግዚአብሔር ቤት ቀድሞ በነበረበት ቦታ እንደ ገና ይሠራ’ አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 እነዚህን ዕቃዎች ውሰድ፥ በኢየሩሳሌምም ባለው መቅደስ አስቀምጠው የእግዚአብሔርም ቤት በስፍራው ይሠራ’” አለው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ‘ይህን ዕቃ ይዘህ ሂድ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ባለው መቅ​ደስ በቦ​ታው አኑ​ረው፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት በስ​ፍ​ራው ይሠራ’ አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 “ይህን ዕቃ ይዘህ ሂድ፤ በኢየሩሳሌምም ባለው መቅደስ አኑረው፤ የእግዚአብሔርም ቤት በስፍራው ይሠራ” አለው።

Ver Capítulo Copiar




ዕዝራ 5:15
5 Referencias Cruzadas  

የፋርስ ንጉሠ ነገሥትም በዐዋጅ የሰጠው ትእዛዝ እንዲህ የሚል ነበር፦ “የሰማይ አምላክ እግዚአብሔር የዓለም ሁሉ ገዢ አድርጎኛል፤ እርሱም ቤተ መቅደስን በይሁዳ ምድር በምትገኘው በኢየሩሳሌም እንድሠራለት አዞኛል።


የተመለሱት ምርኮኞች በምድሪቱ ከሚኖሩት አሕዛብ ተቃውሞ የተነሣ ፍርሀት ቢያድርባቸውም እንኳ መሠዊያውን በዚያው ቀድሞ በቆመበት ቦታ መልሰው ሠሩት፤ ከዚያም በኋላ የሚቃጠል መሥዋዕት ዘወትር ጠዋትና ማታ በዚያ ላይ እንደገና ማቅረብ ጀመሩ።


ናቡከደነፆር በዚሁ በኢየሩሳሌም ተሠርቶ ከነበረው ከቀድሞው ቤተ መቅደስ ማርኮ የወሰዳቸውንና በባቢሎን ማምለኪያ ስፍራው ውስጥ ያኖራቸውን ከወርቅና ከብር የተሠሩ ንዋያተ ቅድሳትም ሁሉ ቂሮስ መልሶ አስረክቦናል፤ ንዋያተ ቅድሳቱንም ያስረከበን የይሁዳ ገዢ አድርጎ በሾመው ሼሽባጻር ተብሎ በሚጠራው ሰው አማካይነት ነው።


ስለዚህም ሼሽባጻር መጥቶ መሠረቱን ጣለ፤ ከዚያም በኋላ የሕንጻው ሥራ እንዲቀጥል ተደርጎ፥ ይኸው እስከ አሁን በመሠራት ላይ ነው፤ ነገር ግን የቤተ መቅደሱ ሕንጻ ገና አልተፈጸመም።’


“ቂሮስ ንጉሠ ነገሥት በሆነ በመጀመሪያው ዓመት በኢየሩሳሌም የነበረው ቤተ መቅደስ የሚቃጠለውና ሌላውም ልዩ ልዩ መሥዋዕት ይቀርብበት ዘንድ እንደገና እንዲሠራ በመፍቀድ ትእዛዝ ሰጥቶአል፤ የቤተ መቅደሱም ርዝመት ኻያ ሰባት ሜትር፥ ስፋቱም ኻያ ሰባት ሜትር መሆን አለበት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos