ይኸውም እኔ በመካከላቸው ከምኖረው ከከነዓናውያን ሴቶች ልጆች መካከል ለልጄ ሚስት እንዳትመርጥ በሰማይና በምድር አምላክ በእግዚአብሔር ስም ማልልኝ፤
ዕዝራ 5:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እነርሱም እንዲህ ሲሉ አስረድተውናል፤ ‘እኛ ሰማይንና ምድርን የፈጠረ የታላቁ እግዚአብሔር አገልጋዮች ነን፤ ስለዚህም ለእርሱ ከብዙ ዘመን በፊት በአንድ ታላቅ የእስራኤል ንጉሥ ተሠርቶለት የነበረውን ቤተ መቅደስና ቅጽር እንደገና መልሰን በመሥራት ላይ እንገኛለን፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰጡን መልስ ይህ ነው፤ “እኛ የሰማይና የምድር አምላክ አገልጋዮች ነን፤ አሁንም እንደ ገና የምንሠራው ቤተ መቅደስ፣ ከብዙ ዘመናት በፊት ታላቁ የእስራኤል ንጉሥ ሠርቶ የጨረሰውን ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የመለሱልን መልስ ይህ ነው፦ ‘እኛ የሰማያትና የምድር አምላክ አገልጋዮች ነን፥ ከብዙም ዘመን ጀምሮ ተሠርቶ የነበረ፥ ታላቅ የእሥራኤል ንጉሥ ሠርቶ የፈጸመውን ቤት እንሠራለን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደዚህም ብለው መለሱልን፦ እኛ የሰማይና የምድር አምላክ ባሪያዎች ነን፥ ከብዙም ዘመን ጀምሮ ተሠርቶ የነበረውን፥ ታላቁም የእስራኤል ንጉሥ ሠርቶ ፈጽሞላቸው የነበረውን ቤት እንሠራለን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንደዚህም ብለው መለሱልን፦ ‘እኛ የሰማይና የምድር አምላክ ባሪያዎች ነን፤ ከብዙም ዘመን ጀምሮ ተሠርቶ የነበረውን፥ ታላቁም የእሥራኤል ንጉሥ ሠርቶ የፈጸመውን ቤት እንሠራለን። |
ይኸውም እኔ በመካከላቸው ከምኖረው ከከነዓናውያን ሴቶች ልጆች መካከል ለልጄ ሚስት እንዳትመርጥ በሰማይና በምድር አምላክ በእግዚአብሔር ስም ማልልኝ፤
ሰሎሞን በነገሠ በዐሥራ አንደኛ ዓመቱ፥ ቡል ተብሎ በሚጠራው በስምንተኛው ወር ላይ የቤተ መቅደሱ ሥራ ልክ በታቀደው መሠረት ሙሉ በሙሉ ተጠናቀቀ፤ ሰሎሞን ቤተ መቅደሱን ለመሥራት የፈጀበት ጊዜ ሰባት ዓመት ነበር።
ናቡከደነፆር ወደሚነደው የእሳት ነበልባል ጒድጓድ ተጠግቶ “የልዑል አምላክ አገልጋዮች የሆናችሁ እናንተ ሲድራቅ፥ ሚሳቅና አብደናጎ ሆይ! ወጥታችሁ ወደዚህ ኑ!” በማለት ተጣራ፤ እነርሱም ከእሳቱ ወጡ።
እኔ በወንጌል ቃል አላፍርም፤ የወንጌል ቃል በመጀመሪያ አይሁድን፥ ቀጥሎም አሕዛብን፥ እንዲሁም የሚያምኑትን ሰዎች ሁሉ ማዳን የሚችል የእግዚአብሔር ኀይል ነው።
ለአንድ ሰው አገልጋዮች ሆናችሁ ለመታዘዝ ራሳችሁን ስታቀርቡ ለዚያ ለምትታዘዙለት ሰው አገልጋዮች መሆናችሁን ታውቃላችሁ፤ እንዲሁም ለኃጢአት ብትታዘዙ ሞትን ለሚያመጣባችሁ ኃጢአት አገልጋዮች ትሆናላችሁ፤ ለእግዚአብሔር ብትታዘዙ ግን ጽድቅን ታገኛላችሁ።
ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር በሌላ መመካት ከእኔ ይራቅ፤ በዚህም መስቀል ዓለም ከእኔ ተለይቶአል፤ እኔም ከዓለም ተለይቼአለሁ።
እርሱን ማምለክ መልካም መስሎ ካልታያችሁ ግን የቀድሞ አባቶቻችሁ ከኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ በነበሩበት ጊዜ ያመልኩአቸው የነበሩትን ወይም አሁን በምድራቸው የምትኖሩባቸውን የአሞራውያንን አማልክት ታመልኩ እንደሆን የምታመልኩትን ዛሬውኑ ምረጡ፤ እኔና ቤተሰቤ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን።”