ከዚህም በኋላ ከዔላም ጐሣ የየሒኤል ልጅ ሸካንያ ዕዝራን እንዲህ አለው፦ “በእርግጥ እኛ በአካባቢአችን ካሉት አሕዛብ ባዕዳን ሴቶችን በማግባት በእግዚአብሔር ላይ የነበረንን እምነት አጓድለናል፤ ይህም ሁሉ ሆኖ አሁንም ለእስራኤል ተስፋ አለ።
ዕዝራ 10:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዔላም ጐሣ፦ ማታንያ፥ ዘካርያስ የሒኤል፥ ዐብዲ፥ የሬሞትና ኤልያ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከኤላም ዘሮች፤ መታንያ፣ ዘካርያስ፣ ይሒኤል፣ አብዲ፣ ይሬሞትና ኤልያ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዔላም ልጆችም፦ ማታንያ፥ ዘካርያ፥ ይሒኤል፥ ዓብዲ፥ የሬሞትና ኤሊያ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከኤላም ልጆችም መታንያ፥ ዘካርያስ፥ ኢያኤል፥ አብዲ፥ ይሬሞት፥ ኤልያ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከኤላም ልጆችም፤ መታንያ፥ ዘካርያስ፥ ይሒኤል፥ አብዲ፥ ይሬሞት፥ ኤልያ። |
ከዚህም በኋላ ከዔላም ጐሣ የየሒኤል ልጅ ሸካንያ ዕዝራን እንዲህ አለው፦ “በእርግጥ እኛ በአካባቢአችን ካሉት አሕዛብ ባዕዳን ሴቶችን በማግባት በእግዚአብሔር ላይ የነበረንን እምነት አጓድለናል፤ ይህም ሁሉ ሆኖ አሁንም ለእስራኤል ተስፋ አለ።