ዕዝራ 1:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእናንተ መካከል የእግዚአብሔር ሕዝብ የሆነ ሁሉ፥ አምላኩ ከእርሱ ጋር ይሁን፤ በይሁዳ ወደሚገኘው ወደ ኢየሩሳሌም ይውጣና የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ይሥራ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሕዝቡ መካከል በእናንተ ዘንድ የሚገኝ ማንኛውም ሰው አምላኩ ከርሱ ጋራ ይሁን፤ በይሁዳ ወደምትገኘው ወደ ኢየሩሳሌም ይውጣና በዚያ ለሚኖረው አምላክ፣ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ይሥራ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሕዝቡ ሁሉ ማንም በእናንተ ውስጥ የሚኖር አምላኩ ከእርሱ ጋር ይሁን፥ እርሱም በይሁዳ ወዳለችው ወደ ኢየሩሳሌም ይውጣ፥ የጌታ የእስራኤል አምላክን ቤት ይሥራ፥ እርሱም በኢየሩሳሌም ያለ አምላክ ነው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሕዝቡ ሁሉ በእናንተ ዘንድ ማንም ቢሆን አምላኩ ከእርሱ ጋር ይሁን፤ እርሱም በይሁዳ ወዳለችው ወደ ኢየሩሳሌም ይውጣ፤ በኢየሩሳሌምም ለሚኖረው አምላክ፥ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ቤትን ይሥራ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሕዝቡ ሁሉ በእናንተ ዘንድ ማንም ቢሆን አምላኩ ከእርሱ ጋር ይሁን፤ እርሱም በይሁዳ ወዳለችው ወደ ኢየሩሳሌም ይውጣ፤ በኢየሩሳሌምም ለሚኖረው አምላክ፥ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ቤት ይሥራ፤ |
እንዲህም አለ፦ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! ለአገልጋዮቹ ቃል ኪዳኑን የሚጠብቅና ከልባቸው ታማኞች እስከ ሆኑ ድረስ ፍቅሩን የሚያጸና በላይ በሰማይ በታችም በምድር እንደ አንተ ያለ አምላክ የለም!
ንጉሥ ዳዊት ለልጁ ለሰሎሞንም እንዲህ አለ፤ “አይዞህ በርታ ሥራውንም በቶሎ ጀምር፤ ምንም ነገር አይግታህ፤ እኔ የማገለግለው እግዚአብሔር አምላክ ከአንተ ጋር ነው፤ ለቤተ መቅደሱ ሥራ ያለህን አገልግሎት እስክትፈጽም ድረስ ከአንተ አይለይም፤ አይተውህም፤ ከቶም አይጥልህም፤
እነዚህ ከሞት የተረፉት ሰዎች በሚመለሱበት ጊዜ በአካባቢአቸው የሚኖሩ ሰዎች ብርና ወርቅ፥ ዕቃና የጭነት ከብቶች ይርዱአቸው፤ ይህም በኢየሩሳሌም ለሚገኘው ቤተ መቅደስ በፈቃዳቸው ከሚሰጡት መባ ሌላ ነው።”
ነገር ግን ዘሩባቤል፥ ኢያሱና የጐሣ መሪዎች ሁሉ እነዚህን ሰዎች፦ “ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ስለምንሠራው ቤተ መቅደስ የእናንተ ርዳታ አያስፈልገንም፤ የፋርስ ንጉሠ ነገሥት ቂሮስ ባዘዘን መሠረት እኛው ራሳችን እንሠራዋለን” ሲሉ መለሱላቸው።
ከዚህም በኋላ ቂሮስ የባቢሎን ንጉሠ ነገሥት በሆነ በመጀመሪያው ዓመት ይህን ቤተ መቅደስ መልሰን መሥራት እንድንችል በዐዋጅ የፈቀደልን ንጉሠ ነገሥቱ ቂሮስ ራሱ ነው።
በዚያን ጊዜ የኤፍራጥስ ምዕራባዊ ክፍል ገዢ የነበረው ታተናይና ሽታርቦዝናይ እንዲሁም ተባባሪዎቻቸው የሆኑ ባለሥልጣኖች ወደ ኢየሩሳሌም መጥተው፦ “ይህን ቤተ መቅደስ ለመሥራትና ቅጽሩንም ለማደስ ማን ፈቀደላችሁ?” ሲሉ ጠየቁአቸው።
ሥራውን ከማደናቀፍ ተቈጠቡ፤ የይሁዳ ክፍለ ሀገር ገዢና የአይሁድ መሪዎች ቀድሞ በነበረበት ስፍራ ላይ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ መልሰው ይሥሩ።
“የሠራዊት ጌታ የእስራኤል አምላክ ሆይ! በኪሩቤል ላይ ዙፋን የዘረጋ አምላክ አንተ ብቻ ነህ፤ የዓለምም መንግሥታት ሁሉ አምላክ አንተ ነህ፤ ሰማይና ምድርን የፈጠርክ አንተ ነህ።
ቂሮስን ‘የመንጋዬ እረኛ ነህ፤ ዕቅዴን ሁሉ ትፈጽማለህ’ እለዋለሁ፤ ኢየሩሳሌምን ‘አንቺ እንደገና ትገነቢአለሽ’ ቤተ መቅደሱን፥ ‘መሠረትህ ይጣላል’ እላቸዋለሁ።”
እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ግን እውነተኛ አምላክ ነህ፤ አንተ ሕያው አምላክ፥ ዘለዓለማዊ ንጉሥ ነህ፤ አንተ በምትቈጣበት ጊዜ ዓለም ይናወጣል፤ የአሕዛብ መንግሥታትም የአንተን ቊጣ ችለው አይቆሙም።
ንጉሡም ዳንኤልን “የአንተ አምላክ ከአማልክት ሁሉ የሚበልጥ አምላክ ነው፤ የነገሥታት ሁሉ ጌታ ነው፥ ምሥጢርንም ሁሉ መግለጥ የሚችል ነው፤ ከዚህም የተነሣ ይህን ታላቅ ምሥጢር ለመግለጥ ችለሃል” አለው።
በመንግሥቴ የሚኖር ሕዝብ ሁሉ የዳንኤልን አምላክ እንዲፈራና እንዲያከብር በዐዋጅ አዝዤአለሁ፤ “እርሱ ሕያውና ዘለዓለማዊ አምላክ ነው፤ መንግሥቱም የማይጠፋ ነው፤ ለመንግሥቱም ፍጻሜ የለውም፤
እግዚአብሔር ለእስራኤል ሕዝብ ቃሉን መላኩ የታወቀ ነው፤ በሁሉ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ሰላምን እየሰበከ የመጣውም ለእነርሱ ነው።