ዘፀአት 9:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደማንኛውም ግብጻዊ እነርሱም ቈስለው ስለ ነበረ በዚያን ጊዜ አስማተኞቹ በሙሴ ፊት መቅረብ አልቻሉም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእነርሱና በግብጻውያን ሁሉ ላይ ዕባጭ ወጥቶ ስለ ነበር፣ አስማተኞቹ በሙሴ ፊት መቆም አልቻሉም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብጉንጅ በጠንቋዮቹና በግብጻውያን ሁሉ ላይ ነበር፤ ጠንቋዮቹም ብጉንጅ ስለ ነበረባቸው በሙሴ ፊት መቆም አልቻሉም፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጠንቋዮችም ቍስል ስለ ነበረባቸው በሙሴ ፊት መቆም አልቻሉም፤ ቍስል ጠንቋዮችንና ግብፃውያንን ሁሉ ይዞአቸው ነበርና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጠንቍዮችም ቍስል ስለ ነበረባቸው በሙሴ ፊት መቆም አልቻሉም፤ ቍስል በጠንቍዮችና በግብፃያን ሁሉ ላይ ነበረና። |
የመጀመሪያው መልአክ ሄደና ጽዋውን በምድር ላይ አፈሰሰ፤ የአውሬው ምልክት ባለባቸውና ለአውሬው ምስል በሚሰግዱ ሰዎች ላይ መጥፎና የሚያሠቃይ ቊስል ወጣባቸው።