አንድ የእግዚአብሔር ነቢይ ወደ ንጉሥ አክዓብ ቀርቦ “እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ይህ ነው፤ ‘ሶርያውያን፦ እግዚአብሔር የኮረብቶች አምላክ እንጂ የሜዳዎች አምላክ አይደለም ብለዋል፤ ከዚህም የተነሣ እኔ እጅግ ብዙ በሆነው ሠራዊታቸው ላይ ድልን አቀዳጅሃለሁ፤ አንተና ሕዝብህም እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ’ ” አለው።
ዘፀአት 7:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሁን ግን በሚያደርገው ነገር የእግዚአብሔርን ማንነት በግድ ታውቃለህ፤ እነሆ፥ እኔ በዚህ በትር የአባይን ወንዝ ውሃ እመታለሁ፤ ውሃውም ወደ ደም ይለወጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፤ “እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ በዚህ ታውቃለህ፤ እይ! በዚህች በእጄ በያዝኋት በትር የአባይን ውሃ እመታለሁ፤ ወደ ደምም ይለወጣል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ እንዲህ ይላል፦ እኔ ጌታ እንደሆንሁ በዚህ ታውቃለህ፤ እነሆ እኔ በዓባይ ወንዝ ያለውን ውኃ በእጄ ባለው በትር እመታለሁ፥ ወደ ደምም ይለወጣል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ በዚህ ታውቃለህ፤ እነሆ፥ እኔ የወንዙን ውኃ በእጄ ባለችው በትር እመታለሁ፤ ውኃውም ወደ ደም ይለወጣል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር እንዲህ ይላል እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ በዚህ ታውቃለህ፤ እነሆ እኔ የወንዙን ውኃ በእጄ ባለችው በትር እመታለሁ፤ ውኃውም ተለውጦ ደም ይሆናል። |
አንድ የእግዚአብሔር ነቢይ ወደ ንጉሥ አክዓብ ቀርቦ “እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ይህ ነው፤ ‘ሶርያውያን፦ እግዚአብሔር የኮረብቶች አምላክ እንጂ የሜዳዎች አምላክ አይደለም ብለዋል፤ ከዚህም የተነሣ እኔ እጅግ ብዙ በሆነው ሠራዊታቸው ላይ ድልን አቀዳጅሃለሁ፤ አንተና ሕዝብህም እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ’ ” አለው።
ከዚህም በኋላ ንጉሡ “ከዕብራውያን የሚወለደውን ወንድ ልጅ ሁሉ እያነሣችሁ ዓባይ ወንዝ ውስጥ ጣሉ፤ ሴቶች ልጆች ግን በሕይወት ይኑሩ” ሲል ለሕዝቡ ጥብቅ ትእዛዝ አስተላለፈ።
እንዲሁም እነዚህን ተአምራት ባደረግሁ ጊዜ ግብጻውያንን እንዴት እንደቀጣሁ ለልጆቻችሁና ለልጅ ልጆቻችሁ መንገር ትችሉ ዘንድ ነው፤ በዚህም ዐይነት ሁላችሁም እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።”
እነዚህን ሁለት ተአምራት አይተው ባያምኑና ቃልህንም ባይሰሙ፥ ከዐባይ ወንዝ ጥቂት ውሃ ወስደህ በመሬት ላይ አፍስሰው፤ ከአባይ ወንዝ የወሰድከውም ውሃ በደረቀ ምድር ላይ ወደ ደም ይለወጣል።”
ንጉሡም “ለመሆኑ እግዚአብሔር ማን ነው? የእርሱንስ ትእዛዝ ሰምቼ እስራኤልን የምለቀው ለምንድን ነው? እኔ እግዚአብሔርን አላውቅም፤ እስራኤልንም አለቅም” አለ።
የእኔ ሕዝብ አደርጋችኋለሁ፤ እኔም አምላካችሁ እሆናለሁ፤ ከግብጽ ባርነትም ነጻ በማወጣችሁ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ መሆኔን ታውቃላችሁ፤
ሙሴና አሮንም እግዚአብሔር እንዳዘዛቸው አደረጉ፤ አሮንም በንጉሡና በመኳንንቱ ፊት በትሩን አንሥቶ የወንዙን ውሃ መታው። የወንዙም ውሃ ተለውጦ ደም ሆነ፤
በዚህ ዐይነት የኀይል ክንዴን በእነርሱ ላይ አንሥቼ እስራኤላውያንን ከአገራቸው በማወጣበት ጊዜ ግብጻውያን እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንኩ ያውቃሉ።”
ግብጽም ባዶዋን ምድረ በዳ ሆና ትቀራለች። በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንኩ ያውቃሉ። “ ‘አንተ የዓባይ ወንዝ የእኔ ነው፤ ይህን ወንዝ የሠራሁት እኔ ነኝ’ ብለሃልና።
እኔ ግብጽን ወና እና ባድማ በማደርግበትና በእርስዋ የሚኖሩትን ሁሉ በማጠፋበት ጊዜ፥ አንተና ሕዝብህ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ፤
በዚህም ዐይነት ታላቅነቴንና ቅድስናዬን አሳያለሁ፤ በብዙ ሕዝቦችም ዘንድ ራሴን አሳውቃለሁ፤ ከዚያ በኋላ እነርሱ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃሉ።”
ተማርከው ወደ ስደት እንዲሄዱ ያደረግኋቸው እኔ ብሆንም እንኳ አሁን ከእነርሱ አንድም ሰው ወደኋላ ሳይቀር ወደ ገዛ አገራቸው እንዲመለሱ አድርጌአለሁ። ስለዚህ ሕዝቤ እኔ እግዚአብሔር አምላካቸው መሆኔን ያውቃሉ።
ውሳኔውም የተላለፈው በቅዱሳን መላእክት ነው፤ ይህም የሆነው ልዑል እግዚአብሔር በምድር መንግሥታት ላይ ሥልጣን ያለው መሆኑን ሁሉም እንዲያውቅ ነው፤ ሥልጣኑንም ለፈቀደለት ሰው ይሰጠዋል፤ የተናቁትንም በሥልጣን ላይ ያስቀምጣቸዋል።’
ከሕዝብ መካከል ተባረህ መኖሪያህ ከዱር አራዊት ጋር ይሆናል፤ ሰባት ዓመት እስኪያልፍ እንደ በሬ ሣር ትበላለህ፤ ይህም የሚሆነው ልዑል እግዚአብሔር በምድር መንግሥታት ሁሉ ላይ ሥልጣን እንዳለውና መንግሥትንም ሁሉ ለወደደው ሰው እንደሚሰጥ እስክትገነዘብ ድረስ ነው።”
“እነሆ፥ እኔ ናቡከደነፆር ለሰማይ ንጉሥ ምስጋና፥ ክብርና ውዳሴ አቀርባለሁ፤ እርሱ የሚያደርገው ነገር ሁሉ ትክክል ነው፤ መንገዱም ፍትሓዊ ነው፤ በትዕቢት የሚመሩትንም ሁሉ ማዋረድ ይችላል።”
ከሕዝብ መካከል ተባረረ፤ አእምሮውም ተለውጦ እንደ እንስሳ ሆነ፤ እንደ በሬም ሣር እየበላ ከሜዳ አህዮች ጋር ሆኖ ለመኖር ተገደደ፤ መጠለያ አጥቶ ሰውነቱ በሰማይ ጠል ረሰረሰ፤ ይህም የሆነው ልዑል እግዚአብሔር በመንግሥታት ሁሉ ላይ ሥልጣን እንዳለውና መንግሥትን ሁሉ ለፈለገው መስጠት እንደሚችል እስከሚረዳበት ጊዜ ድረስ ነበር።
ይልቁንም በሰማይ አምላክ ላይ በመታበይ ራስህን ከፍ ከፍ አደረግህ፤ ከቤተ መቅደሱ ተዘርፈው የመጡትን የወርቅ ዕቃዎች አስመጥተህ አንተና መኳንንቶችህ፥ ሚስቶችህና ቁባቶችህ የወይን ጠጅ መጠጫ አደረጋችኋቸው፤ ከጠጣችሁም በኋላ ማየት ወይም መስማት የማይችሉትንና ምንም ነገር የማያውቁትን ከወርቅ፥ ከብር፥ ከነሐስ፥ ከብረት፥ ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩትን አማልክት አመሰገናችሁ፤ መግደል ወይም ማዳን የሚችለውንና አካሄድህን የሚቈጣጠረውን ሕያው አምላክ ግን አላከበርከውም።
እነርሱ ትንቢት በሚናገሩባቸው በእነዚህ ቀኖች ዝናብ እንዳይዘንብ ሰማይን ለመዝጋት ሥልጣን አላቸው፤ እንዲሁም ውሃዎችን ወደ ደም ለመለወጥና በሚፈልጉትም ጊዜ ሁሉ በማንኛውም ዐይነት መቅሠፍት ምድርን ለመምታት ሥልጣን አላቸው።