ዘፀአት 27:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ከግራር እንጨት መሠዊያ ሥራ፤ ርዝመቱ ሁለት ሜትር ከኻያ ሳንቲ ሜትር የጐኑ ስፋት ሁለት ሜትር ከኻያ ሳንቲ ሜትር ቁመቱም አንድ ሜትር ከሠላሳ ሳንቲ ሜትር ይሁን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ከፍታው ሦስት ክንድ የሆነ መሠዊያ ከግራር ዕንጨት ሥራ፤ ርዝመቱ ዐምስት፣ ወርዱም ዐምስት ክንድ ሆኖ ባለአራት ማእዘን ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ርዝመቱ አምስት ክንድ፥ ወርዱ አምስት ክንድ የሆነ መሠዊያ ከግራር እንጨት ሥራ፤ መሠዊያው አራት ማዕዘን ይሁን፤ ከፍታው ሦስት ክንድ ይሁን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ርዝመቱ አምስት ክንድ፥ ወርዱም አምስት ክንድ መሠዊያን ከማይነቅዝ ዕንጨት አድርግ፤ አራት ማዕዘንም ይሁን፤ ከፍታውም ሦስት ክንድ ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ርዝመቱ አምስት ክንድ፥ ወርዱም አምስት ክንድ መሠዊያ ከግራር እንጨት አድርግ፤ አራት ማዕዘንም ይሁን፤ ከፍታውም ሦስት ክንድ ይሁን። |
ከነሐስ ተሠርቶ ለእግዚአብሔር የተለየውም መሠዊያ በዚያ አዲስ መሠዊያና በቤተ መቅደሱ መካከል ነበር፤ አካዝም ያንን መሠዊያ አስነሥቶ እርሱ ባሠራው በአዲሱ መሠዊያ በስተ ሰሜን በኩል አኖረው፤
አሮንና ዘሮቹ የዕጣን መባና በመሠዊያው ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ሁሉ ያቀርቡ ነበር፤ እንዲሁም በቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ የአምልኮ ሥርዓትና እግዚአብሔር የእስራኤልን ኃጢአት ለሚያስተሰርይበት መሥዋዕት ሁሉ ኀላፊዎች ነበሩ፤ እነርሱም ይህን ሁሉ የሚፈጽሙት እግዚአብሔር ለአገልጋዩ ለሙሴ በሰጠው መመሪያ መሠረት ነው።
የኢዮጼዴቅ ልጅ ኢያሱም ከወገኖቹ ካህናትና የሰላትያል ልጅ ዘሩባቤልም ከዘመዶቹ ጋር በመተባበር የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔርን መሠዊያ እንደገና ሠሩ፤ የእግዚአብሔር ሰው ለሆነው ለሙሴ በተሰጠው የሕግ መጽሐፍ በተጻፈውም መመሪያ መሠረት በዚያ መሠዊያ ላይ የሚቃጠል መሥዋዕት ለማቅረብ ቻሉ።
ሙሴም የእግዚአብሔርን ትእዛዞች ሁሉ ጻፈ፤ በማግስቱም ጠዋት በማለዳ በተራራው ሥር መሠዊያ ሠራ፤ ለእያንዳንዱም የእስራኤል ነገድ አንድ የድንጋይ ዐምድ አኖረ፤
የሚቃጠል መሥዋዕት የሚቀርብበትን መሠዊያ፥ የነሐሱንም መከላከያ መሎጊያዎቹንና የእርሱን መገልገያ ዕቃዎች ሁሉ፥ የመታጠቢያውን ሳሕንና ማስቀመጫውን፥
እዚያም በድንኳኑ መግቢያ ፊት ለፊት የሚቃጠል መሥዋዕት የሚቀርብበትን መሠዊያ አኖረ፤ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቊርባን እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት በእርሱ ላይ አቀረበ፤
የእነርሱም ኀላፊነት በቃል ኪዳኑ ታቦት፥ በገበታው፥ በመቅረዙ፥ በመሠዊያዎቹ፥ ካህናቱ በተቀደሰው ስፍራ በሚገለገሉባቸው ንዋያተ ቅድሳት፥ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን በሚያስገባው መጋረጃ ላይ ሲሆን፥ በአጠቃላይ እነዚህን ነገሮች በሚመለከት አገልግሎት ኀላፊነቱ የእነርሱ ነበር።
በመሠዊያው ላይ ለማገልገል የሚጠቅሙትን ዕቃዎች፥ ማለትም ማንደጃዎችን፥ ሜንጦዎችን፥ መጫሪያዎችንና ጐድጓዳ ሳሕኖችን ያስቀምጡበት፤ የተለፋውንም ስስ ቊርበት በላዩ ደርበው መሎጊያዎችን ያስገቡበት።