Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 39:39 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

39 ከነሐስ የተሠራው መሠዊያ ከነሐስ ከተሠራው መከላከያው ጋር፥ መሎጊያዎቹና የእርሱ መገልገያ ዕቃዎች ሁሉ፥ የመታጠቢያው ሳሕንና ማስቀመጫው፥

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

39 የንሓስ መሠዊያው ከንሓስ መጫሪያው፣ መሎጊያዎቹና ዕቃዎቹ ሁሉ ጋራ፤ የመታጠቢያው ሳሕን ከነማስቀመጫው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

39 የናሱን መሠዊያ፥ የናሱን መከታ፥ መሎጊያዎቹንና ዕቃዎቹን ሁሉ፥ የመታጠቢያውን ሳሕንና ማስቀመጫው፥

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

39 የና​ሱ​ንም መሠ​ዊያ፥ የና​ሱ​ንም መከታ፥ መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም፥ ዕቃ​ው​ንም ሁሉ፥ የመ​ታ​ጠ​ቢ​ያ​ውን ሰንም፥ መቀ​መ​ጫ​ው​ንም፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

39 የናሱንም መሠዊያ፥ የናሱንም መከታ፥ መሎጊያዎቹንም፥ ዕቃውንም ሁሉ፥ የመታጠቢያውን ሰንም መቀመጫውንም፤

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 39:39
7 Referencias Cruzadas  

እንዲሁም በዚያኑ ቀን ከቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት ያለውን አደባባይ መካከለኛ ክፍል ለእግዚአብሔር የተለየ እንዲሆን አደረገ፤ ቀጥሎም በሙሉ የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ የእህል ቊርባንና የኅብረት መሥዋዕት፥ የእንስሶች ስብ ሁሉ ለእግዚአብሔር አቀረበ፤ ይህንንም ያደረገበት ምክንያት ከነሐስ የተሠራው መሠዊያ ይህን ሁሉ መሥዋዕት መያዝ ስለማይችል ነው።


“ከግራር እንጨት መሠዊያ ሥራ፤ ርዝመቱ ሁለት ሜትር ከኻያ ሳንቲ ሜትር የጐኑ ስፋት ሁለት ሜትር ከኻያ ሳንቲ ሜትር ቁመቱም አንድ ሜትር ከሠላሳ ሳንቲ ሜትር ይሁን።


እንደ መረብ ሆኖ የተሠራ የነሐስ መከላከያ አብጅለት፤ ለመከላከያውም አራት የነሐስ ቀለበቶች በአራቱም ማእዘን አድርግለት።


“መታጠቢያ ገንዳ ከነሐስ ሠርተህ፥ እግሮች ባሉት ከነሐስ በተሠራ የሳሕን መቀመጫ ላይ አኑረው፤ እርሱንም በመሠዊያውና በድንኳኑ መካከል አድርገህ ውሃ ጨምርበት።


ወደ መገናኛው ድንኳን መግቢያ የሆነው ደጃፍ የሚቆምባቸውን እግሮች፥ ከነሐስ መከላከያው ጋር የነሐስ መሠዊያውን፥ ለመሠዊያው መገልገያ የሆኑትን ዕቃዎች በሙሉ ከዚህ ነሐስ ሠራ፤


ከወርቅ የተሠራው መሠዊያ፥ የቅባቱ ዘይት፥ ጣፋጭ ሽታ ያለው ዕጣን፥ ለድንኳኑ ደጃፍ የተሠራለት መጋረጃ፥


ለመገናኛው ድንኳን መግቢያ የሚሆኑት መጋረጃዎች፥ ምሰሶዎቹና የሚቆሙባቸው እግሮች፥ ለአደባባዩ መግቢያ የተሠራው መጋረጃና አውታሮቹ፥ ድንኳኑ የሚተከልባቸው ካስማዎች፥ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ የሚገኙ የመገልገያ ዕቃዎች፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos