ዓምራምም አሮንና ሙሴ ተብለው የሚጠሩ ሁለት ወንዶች ልጆችና ማርያም ተብላ የምትጠራ አንዲት ሴት ልጅ ወለደ። አሮንም ናዳብ፥ አቢሁ፥ አልዓዛርና ኢታማር ተብለው የሚጠሩ ወንዶች ልጆች ነበሩት።
ዘፀአት 24:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “አንተ ራስህ፥ አሮን፥ ናዳብ፥ አቢሁና ከእስራኤል መሪዎች ሰባ የሚሆኑት ጭምር እኔ ወዳለሁበት ተራራ ውጡ፤ በሩቅ ሳላችሁም ተንበርክካችሁ ስገዱ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ሙሴን “አንተና አሮን፣ ናዳብና አብዩድ ከሰባዎቹ የእስራኤል አለቆች ጋራ ወደ እግዚአብሔር ኑ፤ ከሩቅም ስገዱ አለው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴንም እንዲህ አለው፦ “አንተ፥ አሮን፥ ናዳብ፥ አቢሁና ከእስራኤልም ሰባ ሽማግሌዎች ወደ ጌታ ውጡ፥ በሩቁም ስገዱ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “አንተ፥ አሮንም፥ ናዳብም፥ አብዩድም፥ ከእስራኤልም ሰባ ሽማግሌዎች ወደ እግዚአብሔር ውጡ፤ በሩቁም ለእግዚአብሔር ስገዱ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴንም፦ አንተ አሮንም ናዳብም አብዩድም ከእስራኤልም ሰባ ሽማግሌዎች ወደ እግዚአብሔር ውጡ፥ በሩቁም ስገዱ፤ |
ዓምራምም አሮንና ሙሴ ተብለው የሚጠሩ ሁለት ወንዶች ልጆችና ማርያም ተብላ የምትጠራ አንዲት ሴት ልጅ ወለደ። አሮንም ናዳብ፥ አቢሁ፥ አልዓዛርና ኢታማር ተብለው የሚጠሩ ወንዶች ልጆች ነበሩት።
እግዚአብሔርም “ውረድና አሮንን ይዘህ ና፤ ካህናቱም ሆኑ ሕዝቡ ወደ እኔ ለመውጣት ወሰኑን ማለፍ የለባቸውም፤ ይህን ቢያደርጉ ግን እኔ እግዚአብሔር እቀጣቸዋለሁ።”
እግዚአብሔርም ሙሴን “እኔ ግዙፍ በሆነ ደመና ወደ አንተ እመጣለሁ፤ ስለዚህም ሕዝቡ እኔ ከአንተ ጋር ስነጋገር በመስማት ከአሁን ጀምሮ አንተ የምትለውን ሁሉ ያምናሉ።” ሙሴም ሕዝቡ የሰጠውን መልስ ወደ እግዚአብሔር አቀረበ፤
“ወንድምህን አሮንንና ልጆቹን ናዳብን፥ አቢሁን፥ አልዓዛርንና ኢታማርን ወደ አንተ አቅርብ፤ ካህናት ሆነው ያገለግሉኝም ዘንድ ከእስራኤል ሕዝብ መካከል ለያቸው።
አሮን የነአሶን እኅት የሆነችውን የዓሚናዳብን ልጅ ኤሊሼባን አገባ፤ እርስዋም ናዳብ፥ አቢሁ፥ አልዓዛርና ኢታማር የተባሉትን ወንዶች ልጆች ወለደችለት።
የሻፋንን ልጅ አዛንያን ጨምሮ ሰባ የእስራኤላውያን መሪዎች በዚያ ነበሩ፤ እያንዳንዱም ጥና ይዞ ነበር፤ ከጥናውም መልካም መዓዛ ያለው የዕጣን ጢስ ይወጣ ነበር፤
እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ለሕዝብ አመራር በመስጠት የታወቁ ሰባ ሽማግሌዎችን ምረጥ፤ እነርሱንም ሰብስበህ ወደ መገናኛው ድንኳን አምጣቸውና በአጠገብህ ይቁሙ፤
ከዚህ በኋላ ጌታ፥ ሌሎች ሰባ ሁለት ሰዎችን መረጠ፤ እርሱ ሊሄድበት ወደአሰበውም ከተማና ቦታ ሁሉ ቀድመውት እንዲሄዱ ሁለት ሁለት አድርጎ ላካቸው።
ሰባ ሁለቱ ደቀ መዛሙርት ከተላኩበት በጣም ደስ ብሎአቸው ተመለሱ፤ ወደ ኢየሱስም ቀርበው፦ “ጌታ ሆይ! በአንተ ስም አጋንንት እንኳ ታዘውልናል” አሉት።
ስለዚህም ከእያንዳንዱ ነገድ የመረጣችኋቸውን የሥራ ልምድ ያላቸውን ዐዋቂዎች መሪዎች ተቀብዬ ሾምኩላችሁ። ከእነርሱም አንዳንዶቹ የሺህ አለቆች፥ አንዳንዶቹ የመቶ አለቆች፥ አንዳንዶቹም የኀምሳና የዐሥር አለቆች ሆነው የተሾሙ ነበሩ። ለነገዶችም ሁሉ ሌሎችንም ሹማምንት ሾምኩ።