በዚያን ዕለት እግዚአብሔር ለአብራም እንዲህ በማለት ቃል ኪዳን ገባለት፦ “ከግብጽ ወንዝ ጀምሮ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ያለውን ምድር ሁሉ ለዘሮችህ እሰጣለሁ፤
ዘፀአት 13:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እግዚአብሔር ለእናንተና ለቀድሞ አባቶቻችሁ ለመስጠት ቃል ወደገባላችሁ ወደ ከነዓናውያን ምድር ያመጣችኋል፤ ይህችንም ምድር በሚያወርሳችሁ ጊዜ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እግዚአብሔር ለእናንተና ለቀደሙት አባቶቻችሁ በመሐላ በሰጠው ተስፋ መሠረት ወደ ከነዓናውያን አገር በሚያስገባችሁና ምድሪቱንም ለእናንተ በሚሰጣችሁ ጊዜ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ለአንተና ለአባቶችህም እንደማለ ወደ ከነዓናውያን ምድር ያመጣሃል ለአንተም ይሰጥሃል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እግዚአብሔርም ለአባቶችህ እንደማለ ወደ ከነዓናውያን ምድር በአገባህ ጊዜ፥ እርስዋንም ለአንተ በሰጠህ ጊዜ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ለአንተ፥ ለአባቶችህም እንደ ማለ ወደ ከነዓናውያን ምድር ባገባህ ጊዜ፥ እርስዋንም በሰጠህ ጊዜ፦ |
በዚያን ዕለት እግዚአብሔር ለአብራም እንዲህ በማለት ቃል ኪዳን ገባለት፦ “ከግብጽ ወንዝ ጀምሮ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ያለውን ምድር ሁሉ ለዘሮችህ እሰጣለሁ፤
አሁን በእንግድነት የምትኖርባትን ይህችን ምድር ለአንተና ለዘርህ እሰጣችኋለሁ፤ መላውን የከነዓን ምድር ለዘለዓለም እንዲወርሱት ለዘርህ እሰጣለሁ፤ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ።”
አይዞህ፥ እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፤ በምትሄድበትም ስፍራ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፤ ወደዚህም ምድር በደኅና እመልስሃለሁ፤ የገባሁልህን ቃል ኪዳን ሁሉ እፈጽምልሃለሁ፤ ከቶም አልተውህም።”
የከነዓናውያንን፥ የሒታውያንን፥ የአሞራውያንን፥ የሒዋውያንንና የኢያቡሳውያንን ምድር እንደሚያወርሳችሁ እግዚአብሔር ለቀድሞ አባቶቻችሁ በመሐላ ቃል ኪዳን ገብቶአል፤ በማርና በወተት ወደ በለጸገችው ወደዚያች ለም ምድር በሚያገባችሁ ጊዜ በዓመቱ መጀመሪያ ወር ላይ ይህን በዓል ታከብሩታላችሁ።
አገልጋዮችህን አብርሃምን፥ ይስሐቅንና ያዕቆብን አስብ፤ ዘራቸውን እንደ ሰማይ ከዋክብት ልታበዛውና የተስፋይቱንም ምድር ርስት ለዘለዓለም አድርገህ ልትሰጣቸው በመሐላ የገባህላቸውንም ቃል ኪዳን አስብ።”
ጡት የሚጠባውን ሕፃን አንዲት ሞግዚት እንደምትታቀፈው እኔም እነርሱን ታቅፌ አንተ ለአባቶቻቸው በመሐላ ቃል ወደ ገባህላቸው ምድር እንዳደርሳቸው የምታደርገኝ እነዚህን ሰዎች እኔ ፀነስኳቸውን? ወይስ እኔ ወለድኳቸውን?