ዘፀአት 10:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም ሙሴን “አንበጦችን ለማምጣት እጅህን በግብጽ ምድር ላይ ዘርጋ፤ እነርሱም መጥተው ቡቃያውን ሁሉና ከበረዶ የተረፈውን ተክል ሁሉ ይበላሉ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሙሴን፣ “የአንበጣ መንጋ ምድሪቱን እንዲወርር ከበረዶ የተረፈውን ሁሉና በማሳም ላይ የበቀለውን ሁሉ ጠርጎ እንዲበላ እጅህን በግብጽ አገር ላይ ዘርጋ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም ሙሴን፦ “አንበጣዎቹ በግብጽ ምድር ላይ እንዲመጡ፥ ከበረዶውም የተረፈውን የምድርን ቡቃያ ሁሉ እንዲበሉ፥ እጅህን በግብጽ ምድር ላይ ዘርጋ” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “በግብፅ ሀገር ላይ እጅህን ዘርጋ፤ አንበጣም በምድር ላይ ይወጣል፤ ከበረዶውም የተረፈውን የምድር ቡቃያ ሁሉና የዛፉን ፍሬ ሁሉ ይበላል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ሙሴን “በግብፅ አገር ላይ እንዲወጡ፥ ከበረዶውም የተረፈውን የምድርን ቡቃያ ሁሉ እንዲበሉ፥ ስለ አንበጣዎች በግብፅ አገር ላይ እጅህን ዘርጋ፤” አለው። |
አገሪቱ ጠቊራ ጨለማ እስክትመስል ድረስ የአንበጣ መንጋ ሸፈናት፤ አንድም ነገር ሳያስቀር ከበረዶ የተረፈውን በየዛፉ ላይ የሚገኘውን ፍሬና ሌላውንም ተክል ሁሉ ግጦ በላው፤ በግብጽ ምድር ከሚገኘው ከማንኛውም ዛፍና ተክል ለምለም የሆነውን ቅጠል ሁሉ መድምዶ በላ።
እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “አሮን በትሩን ወስዶ በግብጽ ምድር በሚገኙት ወንዞች፥ ቦዮችና ኲሬዎች ሁሉ ላይ እንዲዘረጋ ንገረው፤ በዚያን ጊዜ ውሃው ሁሉ ተለውጦ ደም ይሆናል፤ ከእንጨትና ከድንጋይ በተሠሩት የውሃ ማጠራቀሚያ ዕቃዎች እንኳ ሳይቀር በግብጽ ምድር የሚገኘው ውሃ ሁሉ ደም ይሆናል።”