ዘፀአት 1:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አዋላጆቹ እግዚአብሔርን ስለ ፈሩ እግዚአብሔርም ለእነርሱ መልካም ነገር አደረገላቸው፤ ለያንዳንዳቸውም ቤተሰብ ሰጣቸው፤ በዚህም ዐይነት የእስራኤል ሕዝብ በቊጥር እየበዙና ብርቱዎችም እየሆኑ ሄዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህም የተነሣ እግዚአብሔር ለአዋላጆቹ መልካም ሆነላቸው፤ ሕዝቡም በቍጥር እየበዛና እያየለ ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔርም ለአዋላጆቹ መልካም ነገርን አደረገላቸው፤ ሕዝቡም በዛ፥ እጅግም ብርቱ ሆነ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ለአዋላጆች መልካም አደረገላቸው፤ ሕዝቡም በዙ፤ እጅግም ጸኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ለአዋላጆች መልካም አደረገላቸው፤ ሕዝቡም በዛ፤ እጅግም በረታ። |
ነገር ግን እስራኤላውያን በተጨቈኑ መጠን ቊጥራቸው ይበልጥ እየበዛና በምድሪቱም ላይ እየተስፋፉ ሄዱ፤ ከዚህም የተነሣ ግብጻውያን እስራኤላውያንን ፈሩአቸው።
እነርሱም “የዕብራውያን ሴቶች እንደ ግብጻውያን ሴቶች አይደሉም፤ እነርሱ ብርቱዎች ስለ ሆኑ አዋላጆች ወደ እነርሱ ገና ከመምጣታቸው በፊት ያለምንም ችግር ይወልዳሉ” ሲሉ መለሱለት።
ይኸውም ኃጢአተኞች መቶ ጊዜ ወንጀል ቢሠሩም ለረጅም ዘመን ይኖራሉ፤ ይሁን እንጂ እግዚአብሔርን ለሚፈሩና ለሚያከብሩ ሁሉ ነገር እንደሚሰምርላቸው ዐውቃለሁ።
በእውነት እላችኋለሁ፤ የእኔ ደቀ መዝሙር በመሆኑ፥ ከነዚህ ታናናሾች ለአንዱ አንድ ብርጭቆ ቀዝቃዛ ውሃ እንኳ የሚሰጥ ሰው ዋጋውን አያጣም።”
ንጉሡም ‘በእውነት እላችኋለሁ፤ ከእነዚህ ከወንድሞቼ አነስተኛ ለሆነው ለአንዱ እንኳ ያደረጋችኹት ሁሉ ለእኔ እንዳደረጋችሁት ነው!’ ሲል ይመልስላቸዋል።