ያዕቆብም “ጊዜው ገና ቀን ነው፤ መንጋዎቻችሁንም ወደ ቤት የምታስገቡበት ሰዓት ገና አልደረሰም፤ ታዲያ ለምን ውሃ አጠጥታችሁ አታሰማሩአቸውም?” አለ።
ኤፌሶን 5:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህ ዘመን ክፉ ስለ ሆነ በማናቸውም አጋጣሚ ጊዜ ተጠቀሙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀኖቹ ክፉ ናቸውና ዘመኑን በሚገባ ዋጁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን በሚገባ ዋጁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቀኖች ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ። |
ያዕቆብም “ጊዜው ገና ቀን ነው፤ መንጋዎቻችሁንም ወደ ቤት የምታስገቡበት ሰዓት ገና አልደረሰም፤ ታዲያ ለምን ውሃ አጠጥታችሁ አታሰማሩአቸውም?” አለ።
ንጉሡ ይህን በሰማ ጊዜ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እኔ የወሰንኩትን ጥብቅ ውሳኔ ስላወቃችሁ የእናንተ ዕቅድ ነገሩን ለማዘግየት መሆኑን ተረድቼአለሁ፤
ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “አሁን ለጥቂት ጊዜ ከእናንተ ጋር ብርሃን አለ፤ ጨለማ እንዳይደርስባችሁ ብርሃን ሳለላችሁ ተመላለሱ፤ በጨለማ የሚመላለስ ወዴት እንደሚሄድ አያውቅም።
እንግዲህ ከእንቅልፍ የምትነቁበት ሰዓት አሁን መድረሱን ዕወቁ፤ በፊት ካመንበት ጊዜ ይልቅ አሁን የምንድንበት ቀን ይበልጥ ወደ እኛ ቀርቦአል።
ስለዚህ በክፉ ቀን የጠላትን ኀይል ለመቋቋም እንድትችሉና ሁሉንም ፈጽማችሁ ጸንታችሁ ለመቆም እንድትችሉ የእግዚአብሔርን ሙሉ የጦር መሣሪያ አንሡ!