ኤፌሶን 2:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር በመንፈሱ የሚያድርበት ሕንጻ ለመሆን እናንተም አብራችሁ በክርስቶስ ትታነጻላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተም ደግሞ እግዚአብሔር በመንፈሱ የሚኖርበት ማደሪያ ትሆኑ ዘንድ ዐብራችሁ እየተገነባችሁ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእርሱም እናንተ ደግሞ ለእግዚአብሔር መኖሪያ ለመሆን በመንፈስ አብራችሁ ትሠራላችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተ በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ማደሪያ ልትሆኑ በእርሱ ታነጻችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእርሱም እናንተ ደግሞ ለእግዚአብሔር መኖሪያ ለመሆን በመንፈስ አብራችሁ ትሠራላችሁ። |
ሰውነታችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁትና በውስጣችሁም የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ መሆኑን ታውቁ የለምን? እንግዲህ እናንተ የእግዚአብሔር ናችሁ እንጂ የራሳችሁ አይደላችሁም።
የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ከጣዖቶች ጋር ምን ስምምነት አለው? እግዚአብሔርም፦ “መኖሪያዬን በሕዝቤ መካከል አደርጋለሁ፤ ከእነርሱም ጋር እኖራለሁ፤ እኔ አምላካቸው እሆናለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ” ብሎ እንደ ተናገረው እኛ እያንዳንዳችን የሕያው እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነን።
የእግዚአብሔርን ትእዛዝ የሚፈጽሙ ሁሉ በእግዚአብሔር ይኖራሉ፤ እግዚአብሔርም በእነርሱ ይኖራል። እግዚአብሔር በእኛ መኖሩን የምናውቀው እርሱ በሰጠን መንፈስ ነው።
ስለዚህ እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር እናውቃለን፤ እናምናለንም። እግዚአብሔር ፍቅር ነው፤ በፍቅር የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል፤ እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል።