እኛ ሁላችን መሞታችን የማይቀር ነው፤ እኛ በመሬት ላይ እንደ ፈሰሰና ተመልሶም ሊታፈስ እንደማይችል ውሃ ነን፤ እግዚአብሔር ግን በስደት ላይ የሚገኝ ሰው ከእርሱ እንደ ራቀ እንዳይቀር የሚመለስበትን መንገድ ያዘጋጅለታል እንጂ ሕይወቱ በከንቱ እንድትጠፋ አይፈቅድም።
መክብብ 8:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሕይወትን እስትንፋስ ለማስቀረትና የሞትን ቀን ለመለወጥ የሚችል ማንም የለም፤ ማንም ሰው ከጦር ሜዳ መሰናበት እንደማይችል ክፋትም ክፉ ሠሪዎችን አይለቃቸውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰው ነፋስን መቈጣጠር አይችልም፤ በዕለተ ሞቱም ላይ ሥልጣን ያለው ማንም የለም፤ በጦርነት ጊዜ ማንም ከግዴታ ነጻ እንደማይሆን፣ ክፋትም የሚለማመዷትን አትለቃቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መንፈስን ለማገድ በመንፈስ ላይ ሥልጣን ያለው ሰው የለም፥ በሞቱም ቀን ላይ ሥልጣን የለውም፥ በጦርነትም ውስጥ መሰናበቻ የለም፥ ክፋትም ሠሪውን አያድነውም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መንፈስን ለማስቀረት በመንፈሱ ላይ ሥልጣን ያለው ሰው የለም፤ በሞትም ቀን ሥልጣን የለውም፤ በጦርነትም ጊዜ ስንብት የለም፥ ኀጢአትም ሠሪውን አያድነውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መንፈስን ለማስቀረት በመንፈስ ላይ ሥልጣን ያለው ሰው የለም፥ በሞቱም ቀን ሥልጣን የለውም፥ በሰልፍም ስንብቻ የለም፥ ኃጢአትም ሠሪውን አያድነውም። |
እኛ ሁላችን መሞታችን የማይቀር ነው፤ እኛ በመሬት ላይ እንደ ፈሰሰና ተመልሶም ሊታፈስ እንደማይችል ውሃ ነን፤ እግዚአብሔር ግን በስደት ላይ የሚገኝ ሰው ከእርሱ እንደ ራቀ እንዳይቀር የሚመለስበትን መንገድ ያዘጋጅለታል እንጂ ሕይወቱ በከንቱ እንድትጠፋ አይፈቅድም።
ሰዎቹም ከዚያ ተነሥተው እስከ ዮርዳኖስ ወንዝ ድረስ ዘልቀው ሄዱ፤ በየመንገዱም ሶርያውያን ሲሸሹ ጥለውት የሄዱትን ልብስና መሣሪያ ሁሉ አዩ፤ ከዚያም በኋላ ተመልሰው መጥተው ይህን ሁሉ ለንጉሡ ነገሩ።
ይሁን እንጂ እያንዳንዱ ሰው ይህ መጥፎ ዕድል መቼ እንደሚገጥመው አያውቅም፤ ወፍ በራ በወጥመድ ውስጥ እንደምትገባ፥ ዓሣም በመጥፎ አጋጣሚ በመረብ እንደሚያዝ እንዲሁም የሰው ልጅ ሁሉ ሳያስበው ድንገት በሚደርስበት በክፉ አጋጣሚ ይጠመዳል።
“ከሞት ጋር ስምምነት አድርገናል፤ ከሙታንም ዓለም ጋር ቃል ኪዳን ገብተናል” እያላችሁ ትመካላችሁ፤ እንዲሁም “ማታለልን እንደ መጠለያ፥ ሐሰትንም እንደ መጠጊያ አምባ ስላደረግን መቅሠፍት በሚመጣበት ጊዜ ሳይነካን ያልፋል” ብላችሁ ተስፋ ታደርጋላችሁ።
ከሞት ጋር የገባችሁት ስምምነት ይቀራል፤ ከሙታን ዓለም ጋር የገባችሁት ቃል ኪዳን ይፈርሳል፤ መቅሠፍት በድንገት በሚመጣበት ጊዜ መጨረሻችሁ ይሆናል።
እርሱ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ የሞተው በደካማነት ቢሆንም አሁን በእግዚአብሔር ኀይል በሕይወት ይኖራል፤ እኛም ከእርሱ ጋር ደካሞች ሆነናል፤ ከእናንተ ጋር ባለን ግንኙነት ግን ከእርሱ ጋር በእግዚአብሔር ኀይል እንኖራለን።