መክብብ 12:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጠቢባን ንግግር፥ እረኛ የከብቶቹን መንጋ እንደሚነዳበት ጫፉ እንደ ሾለ በትር ነው፤ በአንድነት የተከማቹ ምሳሌዎች ጠልቀው እንደሚገቡ ምስማሮች ናቸው፤ እነርሱም ከሁላችን ጠባቂ ከእግዚአብሔር የተሰጡ ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጠቢባን ቃላት እንደ ሹል የከብት መንጃ ናቸው፤ የተሰበሰቡ አባባሎቹም እጅግ ተቀብቅበው እንደ ገቡ ችንካሮች ሲሆኑ፣ ከአንድ እረኛ የተሰጡ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጠቢባን ቃል እንደ በሬ መውጊያ ነው፥ የተሰበሰቡትም ከአንድ እረኛ የተሰጡት ቃላት እንደ ተቸነከሩ ችንካሮች ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጠቢባን ቃል እንደ በሬ መውጊያ ነው፥ የተሰበሰቡትም ከአንድ እረኛ የተሰጡት ቃላት እንደ ተቸነከሩ ችንካሮች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጠቢባን ቃል እንደ በሬ መውጊያ ነው፥ የተሰበሰቡትም ከአንድ እረኛ የተሰጡት ቃላት እንደ ተቸነከሩ ችንካሮች ናቸው። |
አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ፥ ዐይናችንን አበራህ፤ እነሆ፥ አሁን ደግሞ ለጥቂት ጊዜ በፊትህ ሞገስን አግኝተን ከእኛ ጥቂቶቹ ከባርነት ቀንበር ነጻ ወጥተው በዚህች ቅድስት ምድር በሰላም ይኖሩ ዘንድ ፈቅደሃል፤ ምንም እንኳ በባርነት አገዛዝ ሥር ብንወድቅም እነሆ አዲስ ሕይወት ሰጥተኸናል።
የእስራኤል እረኛ፥ የዮሴፍን ልጆች እንደ መንጋ የምትመራ አምላክ ሆይ! በኪሩቤል ላይ ባለው ዙፋንህ ተቀምጠህ፥ ጸሎታችንን አድምጥ፤ ብርሃንህም ይብራ።
እንደ እረኛ ለመንጋው እንክብካቤ ያደርጋል፤ ግልገሎቹን በአንድነት ይሰበስባል፤ በእጆቹም ዐቅፎ ይወስዳቸዋል፤ እናቶቻቸውንም በርኅራኄ ይመራቸዋል።
ነገር ግን፥ ዮሐንስ ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን ብዙዎች ለመጠመቅ ወደ እርሱ ሲመጡ ባየ ጊዜ፥ እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ የእባብ ልጆች! ከሚመጣው ቊጣ እንድታመልጡ ማን አስጠነቀቃችሁ?
የእግዚአብሔር ቃል ሕያውና የሚሠራ ነው፤ ሁለት አፍ ካለው ሰይፍ ይልቅ ስለታም ነው፤ ነፍስንና መንፈስን፥ ጅማትንና ቅልጥምን እስኪለያይ ድረስ የሚቈራርጥ ነው፤ በልብ ውስጥ የተሰወረውንም ሐሳብና ምኞት መርምሮ የሚፈርድ ነው።