መክብብ 11:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የወጣትነትና የብርቱ ጐልማሳነት ጊዜ ቶሎ ስለሚያልፍ ሐዘንን ከልብህ፥ ጭንቀትንም ከአእምሮህ አስወግድ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ጭንቀትን ከልብህ አርቅ፤ ክፉ ነገርንም ከሰውነትህ አስወግድ፤ ወጣትነትና ጕብዝና ከንቱ ናቸውና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕፃንነትና ጉብዝና ከንቱዎች ናቸውና ከልብህ ጭንቀትን አርቅ፥ ከሰውነትህም ክፉን ነገር አስወግድ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕፃንነትና ጕብዝና፥ አለማወቅም ከንቱ ናቸውና ከልብህ ቍጣን አርቅ፥ ከሰውነትህም ክፉ ነገርን አስወግድ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕፃንነትና ጕብዝና ከንቱዎች ናቸውና ከልብህ ኀዘንን አርቅ፥ ከሰውነትህም ክፉን ነገር አስወግድ። |
የዘመኔን መለኪያ ከእጅ መዳፍ እንዳይበልጥ አድርገህ አሳጠርከው፤ ዕድሜዬም በአንተ ፊት ከምንም አይቈጠርም፤ በእርግጥ የሰው ሕይወት እንደ ነፋስ ሽውታ ነው።
እነሆ በዚህ ዓለም ላይ የተደረገውን ነገር ሁሉ ተመለከትኩ፤ ይሁን እንጂ ሁሉ ነገር ከንቱ ሆኖ አገኘሁት፤ ሁሉም ነገር ነፋስን እንደ መጨበጥ ሆኖ ይቈጠራል።
እንግዲህ ወዳጆቼ ሆይ፥ ይህ ሁሉ ተስፋ የተሰጠው ለእኛ ስለ ሆነ ሥጋንና መንፈስን ከሚያረክስ ከማናቸውም ነገር ራሳችንን እናንጻ፤ እግዚአብሔርንም በመፍራት ቅድስናችን ፍጹም እንዲሆን እናድርግ።