መክብብ 10:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እባብ ከነከሰህ በኋላ የእባብ ማፍዘዣ ድግምት ምንም አይጠቅምህም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እባብ በድግምት ከመፍዘዙ በፊት ቢነድፍ፣ ለደጋሚው ምንም አይጠቅመውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደጋሚ ሳይደግምባት እባብ ብትነድፍ ለደጋሚው ትርፍ የለውም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እባብ ቢነድፍ ባለ መድኀኒትም ባያድን ባለ መድኀኒቱ አይጠቀምም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደጋሚ ሳይደግምባት እባብ ብትነድፍ ለደጋሚው ትርፍ የለውም። |
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ተጠንቀቁ! እነሆ የአስማተኛ ድግምት ሊገታቸው የማይችል መርዘኛ እባቦችንና እፉኝቶችን በመካከላችሁ እልካለሁ፤ እነርሱም ይነድፉአችኋል።”
ምላስም እንደ እሳት ናት፤ ምላስ በአካል ክፍሎቻችን መካከል የምትገኝ ክፉ ዓለም ናት፤ አካላችንን ትበክላለች፤ ከገሃነም እንደሚወጣ እሳትም የኑሮአችንን ሂደት ሁሉ ታቃጥላለች።