ዘዳግም 9:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እንደገናም በታብዔራ፥ በማሳህና በቂብሮት ሐታዋ እግዚአብሔርን አስቈጣችሁት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በተቤራም፣ በማሳህና በቂብሮት ሃታአባ እግዚአብሔርን አስቈጣችሁት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እንደገና በታቤራ፥ በማሳህም፥ በቂብሮት ሐታዋም ጌታን አስቆጣችሁት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በውዕየት፥ በፈተናም በምኞት መቃብርም እግዚአብሔርን አስቈጣችሁት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በተቤራም በማሳህም በምኞት መቃብርም እግዚአብሔርን አስቆጣችሁት። |
ስለዚህም “የምንጠጣው ውሃ ስጠን” ብለው በሙሴ ላይ አጒረመረሙ። ሙሴም “ስለምን ትወቅሱኛላችሁ? ስለምንስ እግዚአብሔርን ትፈታተናላችሁ?” አላቸው።
እስራኤላውያን “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው ወይስ አይደለም?” በማለት በማጒረምረማቸውና እግዚአብሔርን በመፈታተናቸው ያ ስፍራ ማሳህና እና መሪባ ተብሎ ተጠራ።
ሙሴም አሮንን እንዲህ አለው፦ “የአንተን ጥና ወስደህ ከመሠዊያው የእሳት ፍም ጨምርበት፤ በፍሙም ላይ ዕጣን አድርግበት፤ ከዚያም ወደ ሕዝቡ በፍጥነት በመሄድ አስተስርይላቸው፤ ፍጠን! እነሆ፥ የእግዚአብሔር ቊጣ ከመገለጡ የተነሣ በሕዝቡ መካከል መቅሠፍት ጀምሮአል።”
ስለ ሌዊም ነገድ እንዲህ አለ፦ “ጌታ ሆይ! በቱሚምና በዑሪም አማካይነት በማሳና በመሪባ ውሃ ዘንድ ተከራክረህ ለፈተንካቸው ለአገልጋዮችህ ለሌዋውያን ፈቃድህን ግለጥ።