ዘዳግም 8:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እግዚአብሔር አምላክህን በመርሳት፥ እኔ ዛሬ የማዝህን ትእዛዞች፥ ደንቦችና ሥርዓቶች እንዳታፈርስ ተጠንቀቅ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዛሬዪቱ ዕለት የምሰጥህን ትእዛዙን፣ ሕጉንና ሥርዐቱን ባለመጠበቅ አምላክህን እግዚአብሔርን እንዳትረሳው ተጠንቀቅ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ዛሬ እኔ አንተን የማዘውን ትእዛዞቹንና ፍርዱን ሥርዓቱንም ባለመጠበቅ፥ ጌታ አምላክህን እንዳትረሳ ተጠንቀቅ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ዛሬ እኔ አንተን የማዝዘውን ትእዛዙንና ፍርዱን፥ ሥርዐቱንም ባለመጠበቅ አምላክህን እግዚአብሔርን እንዳትረሳ ተጠንቀቅ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዛሬ እኔ አንተን የማዝዘውን ትእዛዙንና ፍርዱን ሥርዓቱንም ባለመጠበቅ አምላክህን እግዚአብሔርን እንዳትረሳ ተጠንቀቅ፤ |
ብዙ ሀብት ቢኖረኝ “እግዚአብሔር ማን ነው?” ብዬ አንተን እስከ መካድ እደርሳለሁ፤ ድኻ ብሆን ደግሞ እሰርቅ ይሆናል፤ በዚህም ሁኔታ የአንተን የአምላኬን ስም አሰድባለሁ።
ምድርን የመሠረተና ሰማያትን የዘረጋ ፈጣሪአችሁን እግዚአብሔርን ረስታችኋል፤ ሊያጠፉአችሁ ከተዘጋጁ ከጨቋኞቻችሁ ቊጣ የተነሣ፥ ዘወትር በፍርሃት ትኖራላችሁ። የእነርሱስ ቊጣ የት አለ?
ዘርፎቹም እንደማስታወሻ ሆነው ስለሚያገለግሉ፥ እነርሱን በምታዩበት ጊዜ ሁሉ ትእዛዞቼን በማስታወስ ትፈጽማላችሁ፤ ከእኔም ርቃችሁ የገዛ ፈቃዳችሁንና ምኞታችሁን የምትፈጽሙ አትሆኑም፤
ከዚህ በኋላ ሙሴ ለሕዝቡ እንዲህ አለ፤ “እስራኤል ሆይ፥ አሁን እንግዲህ የአባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር ወደሚሰጣችሁ ምድር ገብታችሁ ለመውረስ ያበቃችሁ ዘንድ የማስተምራችሁን ሕግና ሥርዓት አዳምጣችሁ በሥራ ላይ አውሉት።
“እግዚአብሔር አምላኬ እንድነግራችሁ ያዘዘኝን ሕግና ሥርዓት ሁሉ አስተምሬአችኋለሁ፤ እርስዋን ለመውረስ በምትገቡባት ምድር ስትኖሩ እነዚህን ትእዛዞች አክብሩ።
እንግዲህ በምትኖሩበት ዘመን ሁሉ ይህን በዐይናችሁ ያያችሁትን ሁሉ እንዳትረሱና ከአእምሮአችሁ እንዳይጠፋ ተጠንቀቁ። ለልጆቻችሁና ለልጅ ልጆቻችሁም አስተምሩአቸው፤
የምትወርሳቸው ቤቶች አንተ ባላኖርከው መልካም ነገር የተሞሉ ይሆናሉ፤ ያልቈፈርካቸውም የውሃ ጒድጓዶች በዚያ ይገኛሉ፤ እንዲሁም አንተ ያልተከልካቸው የወይን ተክሎችና የወይራ ዛፎች ይገኛሉ፤ እግዚአብሔር ወደዚህች ምድር አስገብቶህ በልተህ በምትጠግብበት ጊዜ፥