ዘዳግም 6:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ ‘ማሳህ’ ተብሎ በሚጠራው ቦታ እንዳደረጋችሁት ዐይነት እግዚአብሔር አምላካችሁን አትፈታተኑ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በማሳህ እንዳደረግኸው እግዚአብሔር አምላክህን አትፈታተነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ ‘በማሳህ’ እንደ ፈተናችሁት ጌታ አምላካችሁን አትፈታተኑት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በፈተና ቀን እንደ ፈተንኸው አምላክህ እግዚአብሔርን አትፈታተነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በማሳህ እንደ ፈተናችሁት አምላካችሁን እግዚአብሔርን አትፈታተኑት። |
ስለዚህም “የምንጠጣው ውሃ ስጠን” ብለው በሙሴ ላይ አጒረመረሙ። ሙሴም “ስለምን ትወቅሱኛላችሁ? ስለምንስ እግዚአብሔርን ትፈታተናላችሁ?” አላቸው።
እስራኤላውያን “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው ወይስ አይደለም?” በማለት በማጒረምረማቸውና እግዚአብሔርን በመፈታተናቸው ያ ስፍራ ማሳህና እና መሪባ ተብሎ ተጠራ።
ስለ ሌዊም ነገድ እንዲህ አለ፦ “ጌታ ሆይ! በቱሚምና በዑሪም አማካይነት በማሳና በመሪባ ውሃ ዘንድ ተከራክረህ ለፈተንካቸው ለአገልጋዮችህ ለሌዋውያን ፈቃድህን ግለጥ።