ዘዳግም 33:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የከተሞችህ በሮች በብረትና በናስ የተጠናከሩ ይሁኑ። በዘመንህ ሁሉ ኀይል ይኑርህ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የደጃፍህ መቀርቀሪያ ብረትና ናስ ይሆናል፤ ኀይልህም በዘመንህ ሁሉ ይኖራል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጫማህ ብረትና ናስ ይሆናል፥ እንደ ዕድሜህ እንዲሁ ኃይልህ ይሆናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጫማህ ብረትና ናስ ይሆናል፤ እንደ ዕድሜህ እንዲሁ ኀይልህ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጫማህ ብረትና ናስ ይሆናል፤ 2 እንደ ዕድሜህ እንዲሁ ኃይልህ ይሆናል። |
እግዚአብሔር መላውን ዓለም አተኲሮ በመመልከት፥ በሙሉ ልባቸው በእርሱ ለሚተማመኑት ሁሉ ብርታትን ይሰጣቸዋል፤ እንግዲህ አንተ የሞኝነት ሥራ ስለ ፈጸምክ ከእንግዲህ ወዲህ ጦርነት አይለይህም፤”
እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ! እኔ አምላክህ ነኝ፥ ተስፋ አትቊረጥ! እኔ አበረታሃለሁ፥ እረዳህማለሁ፤ ድል ነሺ በሆነ ክንዴ እደግፍሃለሁ።
አባቱ ግን አገልጋዮቹን ጠርቶ እንዲህ አለ፦ ‘ቶሎ ብላችሁ ከሁሉ የበለጠውን ልብስ አምጡና አልብሱት! በጣቱ ቀለበት፥ በእግሩም ጫማ አድርጉለት!
በሰው ከሚደርሰው ፈተና በቀር ሌላ ፈተና አልደረሰባችሁም፤ እግዚአብሔር ታማኝ ነው፤ ከአቅማችሁ በላይ የሆነ ፈተና እንዲደርስባችሁ አይፈቅድም፤ በምትፈተኑበትም ጊዜ የምትታገሡበትን ኀይል በመስጠት ከፈተናው የምትወጡበትን መንገድ ያዘጋጅላችኋል።
ይህ ሕግ የባዶ ቃላት ቅንብር አይደለም፤ እርሱ የሕይወታችሁ መሠረት ነው፤ ስለዚህ ለዚህ ቃል ታዛዦች ሁኑ፤ ይህን ብታደርጉ ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ በምትወርሱአት ምድር ለረዥም ዘመን ትኖራላችሁ።”
እግዚአብሔር አምላካችሁ ለዘለዓለም እንድትኖሩባት በሚያወርሳችሁ ምድር ለረጅም ዘመን ትኖሩ ዘንድ ለእናንተና ከእናንተም በኋላ ለልጆቻችሁ መልካም እንዲሆንላቸው እኔ ዛሬ የማዛችሁን ሕጉንና ትእዛዞቹን ጠብቁ።”
ሙሴ በላከኝ ጊዜ እንደ ነበርኩት አሁንም እንደዚያው ብርቱ ነኝ፤ በዚያን ጊዜ ለመዋጋት ለመውጣትና ለመግባት የነበረኝ ጒልበት አሁንም እንደዚያው ነው።