ዘዳግም 33:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለ አሴር ነገድም እንዲህ አለ፦ “አሴር ከሌሎች ነገዶች ሁሉ ይበልጥ የተባረከ ይሁን፤ እርሱም በወንድሞቹ ዘንድ የተወደደ ይሁን፤ ምድሩም በወይራ ዛፍ የበለጸገች ትሁን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለ አሴርም እንዲህ አለ፦ “አሴር ከሌሎች ልጆች ይልቅ የተባረከ ነው፤ በወንድሞቹ ዘንድ ተወዳጅ ይሁን፤ እግሩንም በዘይት ውስጥ ያጥልቅ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ አሴርም እንዲህ አለ፦ “አሴር በልጆች የተባረከ ይሁን፥ በወንድሞቹ የተወደደ ይሁን፥ እግሩንም በዘይት ውስጥ ያጥልቅ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለ አሴርም እንዲህ አለ፦ አሴር ከልጆች የተነሣ የተባረከ ይሁን፤ ለወንድሞቹም የተመረጠ ይሁን፤ እግሩንም በዘይት ያጥባል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለ አሴርም እንዲህ አለ፦ 2 አሴር በልጆች የተባረከ ይሁን፤ 2 በወንድሞቹ የተወደደ ይሁን፤ እግሩንም በዘይት ውስጥ ያጥልቅ። |
እግሮቼ እንኳ በወተት እስኪታጠቡ ድረስ ብዙ ወተት አገኝ ነበር። የወይራ ዛፎቼም በጭንጫ መሬት ላይ እንኳ ተተክለው እንደ ጐርፍ የሚወርድ ብዙ ዘይት ይሰጡኝ ነበር።
የምትጸልዩልኝም በይሁዳ ምድር ካሉት ከማያምኑ ሰዎች እጅ እንድድንና በኢየሩሳሌም ያለኝ አገልግሎትም በእግዚአብሔር ወገኖች ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖረው ነው።