15 ሰማይንና ምድርን የፈጠረ እግዚአብሔር ይባርካችሁ!
15 ሰማይንና ምድርን በፈጠረ፣ በእግዚአብሔር የተባረካችሁ ሁኑ።
15 እናንተ ሰማይንና ምድርን በሠራ ጌታ የተባረካችሁ ሁኑ።
በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማያትንና ምድርን ፈጠረ።
እንዲህ ብሎም አብራምን ባረከው፤ “ሰማይንና ምድርን የፈጠረ ልዑል እግዚአብሔር አብራምን ይባርክ!
ርዳታዬ የሚመጣው ሰማይንና ምድርን ከፈጠረ ከእግዚአብሔር ነው።
ይህንንም ርዳታ ያገኘነው ሰማይንና ምድርን ከፈጠረ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።
ሰማይንና ምድርን የፈጠረ እግዚአብሔር ከጽዮን ይባርካችሁ!
ማዳን የእግዚአብሔር ነው፤ እግዚአብሔር ሆይ፥ በረከትህ በሕዝብህ ላይ ይሁን።
ሌሎች ሕዝቦች የሚሰግዱላቸው አማልክት ጣዖቶች ናቸው፤ እግዚአብሔር ግን ሰማያትን የፈጠረ አምላክ ነው።
“እናንተ ሰዎች ለምን ይህን ታደርጋላችሁ? እኛም እንደ እናንተ ሰዎች ነን፤ እኛ እዚህ የመጣነው እናንተ ከዚህ ከከንቱ ነገር ሁሉ ርቃችሁ ሰማይን፥ ምድርን፥ ባሕርንና በውስጣቸው የሚገኙትን ሁሉ ወደ ፈጠረው ወደ ሕያው አምላክ እንድትመለሱ መልካም ዜና ልናበሥርላችሁ ነው፤
መርቁ እንጂ ክፉውን በክፉ ፈንታ፥ ስድብንም በስድብ ፈንታ አትመልሱ፤ እናንተ የተጠራችሁት ይህን በማድረግ በረከትን ለመውረስ ነው፤
በታላቅ ድምፅም “እግዚአብሔርን ፍሩ! አክብሩትም! የእርሱ የፍርድ ሰዓት ደርሶአል፤ ሰማይንና ምድርን ባሕርንና የውሃ ምንጮችን ለፈጠረ አምላክ ስገዱ!” አለ።