La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘዳግም 32:33 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ወይናቸው እንደ እባብ መርዝ ነው፤ እንደ ክፉ እፉኝትም መርዝ ነው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ወይናቸው የእባብ መርዝ፣ የመራዥ እባብም መርዝ ነው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ወይናቸው የእባብ መርዝ፥ የጨካኝ እፉኝት መርዝ ነው።”

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የወ​ይን ጠጃ​ቸው የእ​ባብ መርዝ፥ የሚ​ገ​ድ​ልም የእ​ፉ​ኝት መርዝ ነው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የወይን ጠጃቸው የእባብ መርዝ፥ 2 የእፉኝትም ሥራይ ነው።

Ver Capítulo



ዘዳግም 32:33
8 Referencias Cruzadas  

ምላሳቸው እንደ መርዛም እባብ ተናዳፊ ነው፤ ቃላቸውም እንደ እፉኝት መርዝ ነው።


እነርሱ እንደ እባብ መርዘኞች ናቸው፤ እንደ ደንቆሮ እፉኝትም ጆሮአቸውን ይደፍናሉ።


እፉኝት ጆሮውን የሚደፍነው የእባብ አፍዛዦችን ድምፅ፥ ወይም የአስማተኞችን ድግምት ላለመስማት ነው።


የእግዚአብሔር ሕዝብ እንዲህ ይላሉ፦ “ዝም ብለን መቀመጣችን ለምንድን ነው? አምላካችን እግዚአብሔር ሞት ፈርዶብናል፤ እርሱን ስለ በደልን የተመረዘ ውሃ እንድንጠጣ አድርጎናል። ኑ! ወደተመሸጉ ከተሞች ሮጠን እዚያ እንሙት፤


ሰውን የሚጐዳ ክፉ ቃል ለመናገር አፋቸው እንደ መቃብር የተከፈተ ነው፤ በምላሳቸው ያታልላሉ፤ የከንፈራቸውም ንግግር እንደ እባብ መርዝ የሚጐዳ ነው፤


ጠላቶቻችን እንደ ሰዶምና ገሞራ የረከሱ ናቸው፤ እነርሱም መራራና መርዘኛ ፍሬ እንደሚሰጥ የወይን ተክል ናቸው።


“ጠላቶቻችን የፈጸሙት በደል በእግዚአብሔር መዝገብ ውስጥ ተመዝግቦ ይገኛል።