ዘዳግም 30:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተም እንደገና ለእርሱ ታዛዥ ትሆናለህ፤ ዛሬ እኔ የምሰጥህንም የእርሱን ትእዛዞች ትጠብቃለህ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንተም ተመልሰህ ለእግዚአብሔር ትታዘዛለህ፤ ዛሬ እኔ የማዝዝህን ትእዛዝ ሁሉ ትጠብቃለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተም ተመልሰህ ለጌታ ቃል ትታዘዛለህ፤ ዛሬ እኔ የማዝህንም ትእዛዝ ሁሉ ታደርጋለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተም ተመልሰህ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል ትሰማለህ፤ ዛሬም እኔ የማዝዝህን ትእዛዙን ሁሉ ታደርጋለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተም ተመልሰህ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል ትሰማለህ፥ ዛሬም እኔ የማዝዝህን ትእዛዙን ሁሉ ታደርጋለህ |
እነሆ ከዚህ ጊዜ በኋላ ከእስራኤል ሕዝብ ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነው፤ ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ፤ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፤ አምላካቸውም እሆናለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ፤
የይሁዳ ሕዝብ በእነርሱ ላይ ላመጣ ያቀድኩትን ጥፋት በሚሰሙበት ጊዜ ምናልባት ከክፉ ሥራቸው ይመለሱ ይሆናል፤ እኔም በደላቸውንና ኃጢአታቸውን ይቅር እላለሁ።”
በምትሠራው ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ያበለጽግሃል፤ ልጆችህን፤ እንስሶችህንና የምድርህን ሰብልና ፍሬ ያበዛልሃል፤ እግዚአብሔር የቀድሞ አባቶችህን በማበልጸግ ደስ ይለው እንደ ነበር አንተንም በማበልጸግ ደስ ይለዋል።