ዘዳግም 29:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደዚህም ስፍራ በደረስን ጊዜ፥ የሐሴቦን ንጉሥ ሲሖንና የባሳን ንጉሥ ዖግ ሊወጉን መጥተውብን ነበር፤ ነገር ግን እኛ ድል አደረግናቸው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደዚህ ስፍራ በደረሳችሁ ጊዜ፣ የሐሴቦን ንጉሥ ሴዎንና የባሳን ንጉሥ ዐግ ሊወጉን መጡ፤ ሆኖም ድል አደረግናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደዚህም ስፍራ በደረሳችሁ ጊዜ፥ የሐሴቦን ንጉሥ ሴዎንና የባሳን ንጉሥ ዐግ ሊወጉን መጡ፤ ነገር ግን ድል አደረግናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሐሴቦን ንጉሥ ሴዎን፥ የባሳንም ንጉሥ ዐግ ሊወጉን ወጡብን፤ እኛም መታናቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደዚህም ስፍራ በመጣችሁ ጊዜ የሐሴቦን ንጉሥ ሴዎን የባሳንም ንጉስ ዐግ ሊወጉን ወጡብን፥ እኛም መታናቸው፤ |
“በሞአብ በኩልም ካለፍን በኋላ እግዚአብሔር እንዲህ አለን፦ ‘አሁን ተነሥታችሁ የአርኖንን ወንዝ ተሻገሩ፤ በሐሴቦን ተቀምጦ የሚገዛውን የአሞራውያንን ንጉሥ ሲሖንን ከነምድሩ ለእናንተ አሳልፌ ሰጥቻችኋለሁ፤ እርሱን ወግታችሁ ምድሩን ውረሱ፤
“ምድሪቱን ከወረስን በኋላ በአርኖን ወንዝ አጠገብ ካለችው ከዓሮዔር ከተማ ጀምሮ በስተ ሰሜን በኩል ያለውን ግዛትና የኮረብታማይቱን የገለዓድን እኩሌታ ከነከተሞችዋ ለሮቤልና ለጋድ ነገዶች ሰጠሁ፤
ለምናሴ ነገድ እኩሌታም ከገለዓድ የተረፈውንና ዖግ ይገዛው የነበረውን ባሳንን በሙሉ ሰጠሁ፤ ይኸውም መላው የአርጎብ ግዛት መሆኑ ነው።” ባሳን የረፋያውያን ምድር በመባል ይታወቅ ነበር፤