Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘዳግም 3:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ለምናሴ ነገድ እኩሌታም ከገለዓድ የተረፈውንና ዖግ ይገዛው የነበረውን ባሳንን በሙሉ ሰጠሁ፤ ይኸውም መላው የአርጎብ ግዛት መሆኑ ነው።” ባሳን የረፋያውያን ምድር በመባል ይታወቅ ነበር፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ቀሪውን የገለዓድ ምድርና የዐግ ግዛት የሆነውን ባሳንን በሙሉ ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ሰጠሁ። በባሳን የሚገኘው መላው የአርጎብ ክልል የራፋይማውያን ምድር በመባል ይታወቅ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ከገለዓድም የቀረውን የዖግንም መንግሥት ባሳንን ሁሉ፥ የአርጎብንም ግዛት ሁሉ ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ሰጠሁ፥ ያቺ ባሳን ሁሉ የራፋይም አገር ተብላ ተጠራች።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ከገ​ለ​ዐ​ድም የቀ​ረ​ውን የዐ​ግን መን​ግ​ሥት ባሳ​ንን ሁሉ፥ የአ​ር​ጎ​ብ​ንም ምድር ሁሉ ለም​ናሴ ነገድ እኩ​ሌታ ሰጠሁ፤ ያችም ባሳን ሁሉ የራ​ፋ​ይም ሀገር ተብላ ተቈ​ጠ​ረች።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ከገለዓድም የቀረውን የዐግንም መንግሥት ባሳንን ሁሉ፥ የአርጎብንም ምድር ሁሉ ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ሰጠሁ፤ ያችም ባሳን ሁሉ የራፋይም አገር ተብላ ተቆጠረች።

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 3:13
10 Referencias Cruzadas  

በዐሥራ አራተኛው ዓመት ከዶርላዖሜርና ከእርሱ ጋር የተባበሩት ነገሥታት ከነሠራዊቶቻቸው መጥተው ረፋያውያንን በዐስታሮት ቃርናይም፥ ዙዛውያንን በሃም፥ ኤማውያንን በሻዌ ቂርያታይም፥


እርሱም የያዘው ግዛት፥ ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተ ምሥራቅ፥ በስተ ደቡብ በኩል ከአርኖን ወንዝ በላይ እስከምትገኘው እስከ ዓሮዔር ከተማ የሚደርስ ሲሆን ይህም የጋድ፥ የሮቤልና በምሥራቅ የሚገኘው የምናሴ ነገድ እኩሌታ ይኖሩባቸው የነበሩትን የገለዓድንና የባሳንን ግዛቶች ያጠቃልላል።


ወደዚህም ስፍራ በደረስን ጊዜ፥ የሐሴቦን ንጉሥ ሲሖንና የባሳን ንጉሥ ዖግ ሊወጉን መጥተውብን ነበር፤ ነገር ግን እኛ ድል አደረግናቸው፤


ምድራቸውንም ወርሰን ለሮቤልና ለጋድ ነገዶች እንዲሁም ለእኩሌታ የምናሴ ነገድ ርስት እንዲሆን አከፋፍለን ሰጥተናል፤


“ምድሪቱን ከወረስን በኋላ በአርኖን ወንዝ አጠገብ ካለችው ከዓሮዔር ከተማ ጀምሮ በስተ ሰሜን በኩል ያለውን ግዛትና የኮረብታማይቱን የገለዓድን እኩሌታ ከነከተሞችዋ ለሮቤልና ለጋድ ነገዶች ሰጠሁ፤


ከምናሴ ነገድ ወገን የሆነው ያኢር መላውን የአርጎብ ምድር ወረሰ፤ ይህችውም እስከ ገሹርና እስከ ማዕካ ጠረፍ የምትደርሰው ባሳን ናት፤ መንደሮቹንም በእርሱ ስም እንዲጠሩ አደረገ፤ ስለዚህ እነርሱ የያኢር መንደሮች ተብለው እስከ ዛሬ ይጠራሉ።


በዚያኑ ጊዜ ከተሞቹን ሁሉ ያዝን፤ ያልወሰድነው ምንም ከተማ አልነበረም፤ በዚህም ዐይነት የባሳን ንጉሥ ዖግ በአርጎብ ግዛት ያስተዳድራቸው የነበሩትን ሥልሳ ከተሞች ወሰድን።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos