ከዚህም በኋላ ናቡዛርዳን በከተማይቱ ቀርተው የነበሩትንና ሌሎችን ሰዎች፥ እንዲሁም ከድተው ወደ ባቢሎናውያን የተጠጉትን ሁሉ ይዞ ወደ ባቢሎን ወሰዳቸው፤
ዘዳግም 28:36 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እግዚአብሔር አንተንና ንጉሥህን ከዚህ በፊት የቀድሞ አባቶችህም ሆኑ አንተ ወዳልነበራችሁበት ባዕድ አገር አፍልሶ ይወስዳችኋል፤ በዚያም ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩ ባዕዳን አማልክትን ታመልካላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር አንተንና በላይህ ያነገሥኸውን ንጉሥ፣ አንተና አባቶችህ ወደማታውቁት ሕዝብ ይወስዳችኋል፤ ከዚያም ከዕንጨትና ከድንጋይ የተሠሩ ሌሎች አማልክትን ታመልካለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ጌታ አንተን በአንተም ላይ የምታነግሠውን ንጉሥ አንተና አባቶችህ ወደማታውቁት ሕዝብ ይወስዳችኋል። በዚያም ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩ ሌሎች አማልክትን ታመልካለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እግዚአብሔርም አንተን፥ በአንተም ላይ የምትሾማቸውን አለቆችህን አንተና አባቶችህ ወዳላወቃችኋቸው ሕዝብ ይወስድሃል፤ በዚያም ሌሎችን የእንጨትና የድንጋይ አማልክትን ታመልካለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም አንተን በአንተም ላይ የምታነግሠውን ንጉሥ አንተና አባቶችህ ወዳላወቃችኋቸው ሕዝብ ይወስድሃል፤ በዚያም ሌሎችን የእንጨትና የድንጋይ አማልክት ታመልካለህ። |
ከዚህም በኋላ ናቡዛርዳን በከተማይቱ ቀርተው የነበሩትንና ሌሎችን ሰዎች፥ እንዲሁም ከድተው ወደ ባቢሎናውያን የተጠጉትን ሁሉ ይዞ ወደ ባቢሎን ወሰዳቸው፤
ስለዚህም የአሦር ሠራዊት ይሁዳን እንዲወር እግዚአብሔር ፈቀደ፤ ሠራዊቱም ምናሴን ማርኮ በአፍንጫው ሥናጋ በማግባት በሰንሰለት አስሮ ወደ ባቢሎን ወሰደው።
ስለዚህ የባቢሎን ንጉሥ በእነርሱ ላይ አደጋ እንዲጥል እግዚአብሔር ፈቀደ፤ ንጉሡም በቤተ መቅደሱ ውስጥ የነበሩትን እንኳ ሳይቀር፥ በይሁዳ የሚገኙትን ወጣቶች ወንዶችን ሁሉ በሰይፍ ፈጀ፤ እግዚአብሔር ለናቡከደነፆር አሳልፎ ስለ ሰጣቸውም ወጣት ወይም ሽማግሌ፥ ወንድ ወይም ሴት ማንንም ሳይለይ፥ ሁሉንም ያለ ምሕረት አጠፋቸው።
በሰይፍ ከመገደል የተረፉትንም ሁሉ ማርኮ ወደ ባቢሎን ወሰዳቸው፤ እነርሱም የፋርስ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት እስከ ተነሣበት ጊዜ ድረስ፥ በዚያው በባቢሎን ባሪያዎች ሆነው፥ ንጉሥ ናቡከደነፆርንና የእርሱን ዘሮች ያገለግሉ ነበር።
ስለዚህ ከዚህች አገር አውጥቼ፥ እናንተም ሆናችሁ የቀድሞ አባቶቻችሁ ወደማያውቁት አገር እወረውራችኋለሁ፤ እዚያም ሐሰተኞች አማልክትን ቀንና ሌሊት ታመልካላችሁ፤ ፈጽሞ ምሕረት አላደርግላችሁም።’ ”
ሴዴቅያስ በይሁዳ በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት በዐሥረኛው ወር የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ከሠራዊቱ ሁሉ ጋር መጥቶ በኢየሩሳሌም ላይ ከበባ አደረገ።
ስለዚህ የእስራኤል አምላክ እኔ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የማደርገውን ነገር ልንገራችሁ፤ ይህ ሕዝብ ምግቡ መራራ መጠጡም የተመረዘ ውሃ እንዲሆንበት አደርጋለሁ።
የቅጽር በሮች ከመሬት በታች ተቀበሩ፤ መወርወሪያዎቻቸውም ተሰባብረው ወደቁ፤ ንጉሡና መሳፍንቱ አሁን በአሕዛብ መካከል በስደት ላይ ናቸው፤ የኦሪት ሕግ ትምህርት ከእንግዲህ ወዲህ አይሰጥም፤ ነቢያትም ከእግዚአብሔር ዘንድ ራእይ አይገለጥላቸውም።
የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! ልዑል እግዚአብሔር ስለ እናንተ እንዲህ ይላል፦ “አሁንም ሆነ ወደፊት የማታዳምጡኝ ከሆነ እያንዳንዳችሁ ሄዳችሁ ጣዖቶቻችሁን አምልኩ! ቅዱስ ስሜን ግን ከእንግዲህ ወዲያ በጣዖቶቻችሁና በመባዎቻችሁ እንድታስነውሩት አልፈቅድም።
“እግዚአብሔር በመላው ዓለም በሕዝቦች መካከል ከአንድ የምድር ዳርቻ እስከ ሌላው ድረስ ይበትንሃል፤ በዚያም አንተም ሆንክ የቀድሞ አባቶችህ ሰግዳችሁላቸው የማታውቁትን ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩትን ባዕዳን አማልክት ታመልካለህ።
እዚያም፥ ለማየት፥ ለመስማት፥ ለመብላትና ለማሽተት የማይችሉትንና ከእንጨትና ከድንጋይ በሰው እጅ የተሠሩትን ሌሎች አማልክትን ታመልካላችሁ።