ዘዳግም 26:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እግዚአብሔር አምላክህ ሕጎችንና ሥርዓቶችን እንድትጠብቅ እነሆ፥ ዛሬ ያዝሃል፤ ስለዚህ በፍጹም ልብህና ነፍስህ ጠብቃቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላክህ እግዚአብሔር ይህን ሥርዐትና ሕግ ትጠብቅ ዘንድ ዛሬ ያዝዝሃል፤ አንተም በፍጹም ልብህ፣ በፍጹምም ነፍስህ ትፈጽመው ዘንድ ተጠንቀቅ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አምላክህ ጌታ ይህን ሥርዓትና ሕግ እንድትጠብቅ ዛሬ ያዝሃል፤ ስለዚህ አንተም በፍጹም ልብህ፥ በፍጹምም ነፍስህ ለመፈጸም ተጠንቀቅ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አምላክህ እግዚአብሔር ይህን ሥርዐትና ፍርድ ታደርግ ዘንድ ዛሬ አዝዞሃል፤ አንተም በፍጹም ልብህና በፍጹም ነፍስህ ጠብቀው፤ አድርገውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምላክህ እግዚአብሔር ይህን ሥርዓትና ፍርድ ታደርግ ዘንድ ዛሬ አዝዞሃል፤ አንተም በፍጹም ልብህና በፍጹም ነፍስህ ጠብቀው፥ አድርገውም። |
“እንግዲህ እስራኤል ሆይ! እግዚአብሔር አምላክህን እንድትፈራው፥ በመንገዱ ሁሉ እንድትሄድ፥ እንድትወደው በሙሉ ልብህና በሙሉ ሐሳብህ እንድታመልከው፥ ለደኅንነትህ ሲባል እኔ ዛሬ የማዝህን የእግዚአብሔር አምላክህን ትእዛዝና ድንጋጌ እንድትጠብቅ ነው እንጂ እርሱ ሌላ ከአንተ ምን ይፈልጋል?
“የቀድሞ አባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር በሚሰጣችሁ ምድር በምትኖሩበት ዘመን ሁሉ በጥንቃቄ የምትጠብቁአቸው ኅጎችና ሥርዓቶች እነዚህ ናቸው፤
እግዚአብሔር አምላክህ መሆኑንና በሕጉም የምትመራ መሆንህን ዛሬ አንተ አረጋግጠሃል፤ ሥርዓቱን፥ ትእዛዞቹንና ሕጎቹን ለመጠበቅና ታዛዥ ለመሆን ቃል ገብተሃል፤
“አሁን ተሻግራችሁ በርስትነት በሚሰጣችሁ ምድር እንድትጠብቁት እግዚአብሔር አምላክህ እንዳስተምርህ ያዘዘኝ ትእዛዞች፥ ሕግና ሥርዓት እነዚህ ናቸው።
አምላክህ እግዚአብሔር የሰጠህን ትእዛዞች ስለ መጠበቅህ በልብህ ያለውን ሐሳብ ያውቅ ዘንድ አንተን ለመፈተን በዚህ በረሓ አርባ ዓመት ሙሉ በመከራ ውስጥ በማሳለፍ እንዴት እንደ መራህ አስታውስ።