ነገር ግን በመከር ጊዜ ከምታመርቱት ከአምስት አንዱን እጅ ለፈርዖን መስጠት አለባችሁ፤ የቀረው አራት አምስተኛው እጅ ግን ለመሬታችሁ ዘር፥ ለራሳችሁና ለልጆቻችሁ ለቤተሰባችሁም ሁሉ ምግብ ይሁናችሁ።”
ዘዳግም 26:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በሦስተኛው ዓመት ማለት ዐሥራት በምታወጣት ዓመት ዐሥራትህን ሁሉ አጠናቅቀህ ከሰበሰብክ በኋላ በከተማህ ለሚገኙ ለሌዋውያን፥ ለመጻተኞች፥ ለሙት ልጆችና ባሎቻቸው ለሞቱባቸው ሴቶች ሰጥተህ ጠግበው እንዲበሉ አድርግ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዐሥራት ዓመት የሆነውን የሦስተኛውን ዓመት ምርት አንድ ዐሥረኛ ለይተህ ካወጣህ በኋላ በየከተሞችህ ውስጥ በልተው እንዲጠግቡ፣ ለሌዋዊው፣ ለመጻተኛው፣ አባት ለሌለውና ለመበለቲቱ ስጣቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አሥራት በምታወጣት በሦስተኛው ዓመት ከምርትህ አንድ ዐሥረኛ ለይተህ ካወጣህ በኋላ በየከተሞችህ ውስጥ በልተው እንዲጠግቡ፥ ለሌዋዊው፥ ለመጻተኛው፥ አባት ለሌለውና ለመበለቲቱ ስጣቸው፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ዐሥራት በምታወጣበት በሦስተኛው ዓመት የምድርህን ፍሬ ሁሉ ዐሥራት አውጥተህ በፈጸምህ ጊዜ፥ ሁለተኛ ዐሥራት አውጥተህ በከተሞችህ ውስጥ ይበሉ ዘንድ፥ ይጠግቡም ዘንድ ለሌዋዊው፥ ለመጻተኛውም፥ ለድሃ-አደጉም፥ ለመበለቲቱም ስጣቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሥራት በምታወጣበት በሦስተኛው ዓመት የፍሬህን ሁሉ አሥራት አውጥተህ በፈጸምህ ጊዜ፥ በአገርህ ደጅ ውስጥ ይበሉ ዘንድ ይጠግቡም ዘንድ ለሌዋዊው ለመጻተኛውም ለድሀ አደጉም ለመበለቲቱም ስጣቸው። |
ነገር ግን በመከር ጊዜ ከምታመርቱት ከአምስት አንዱን እጅ ለፈርዖን መስጠት አለባችሁ፤ የቀረው አራት አምስተኛው እጅ ግን ለመሬታችሁ ዘር፥ ለራሳችሁና ለልጆቻችሁ ለቤተሰባችሁም ሁሉ ምግብ ይሁናችሁ።”
በዚህ ዐይነት ዮሴፍ ከመከር ሁሉ አንድ አምስተኛው እጅ ለፈርዖን እንዲሰጥ የግብጽን መሬት ይዞታ በሚመለከት ሕግ አወጣ፤ ይህም ሕግ እስከ ዛሬ ድረስ ይሠራበታል፤ የፈርዖን ንብረት ያልሆነው የካህናት መሬት ብቻ ነው።
እስራኤላውያን ልዩ መባ አድርገው ለእኔ የሚያመጡትን ዐሥራት ለእነርሱ ስለ መደብኩላቸው፤ በእስራኤል ዘላቂነት ያለው ቋሚ ርስት እንደማይኖራቸው ነግሬአቸዋለሁ።”
እርሱንም ከወንዶችና ከሴቶች ልጆችህ፥ ከወንዶችና ከሴቶች አገልጋዮችህ፥ በከተሞችህ ከሚኖሩት ሌዋውያን፥ በአገርህ ከሚኖሩ መጻተኞች፥ እናትና አባት ከሌላቸው ድኻ አደጎችና ባሎቻቸው ከሞቱባቸው ሴቶች ጋር አብረህ በመሆን ተደሰት።
እንግዲህ መልከጼዴቅ አብርሃምን በተገናኘው ጊዜ ሌዊ ከአባቱ ከአብርሃም ገና ስላልተወለደ ዐሥራትን መቀበል የሚገባው ሌዊ ራሱ በአብርሃም አማካይነት ዐሥራትን ከፍሎአል ማለት ነው።