“ይህን ስጦታ በፈቃደኛነት መስጠት እንችል ዘንድ እኔ ማነኝ? ሕዝቤስ ማነው? ሁሉ ነገር ከአንተ የተቀበልነው ስጦታ ነው፤ እነሆ የአንተ የነበረውንም መልሰን ሰጥተንሃል፤
ዘዳግም 26:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም እነሆ፥ እኔ እርሱ ከሰጠኝ መጀመሪያ የሆነውን በኲራት አምጥቼአለሁ።’ “ከዚህም ቀጥሎ ቅርጫቱን በእግዚአብሔር ፊት በማኖር ስገድ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሁንም እግዚአብሔር ሆይ፤ እነሆ፤ አንተ የሰጠኸኝን የምድሪቱን በኵራት አምጥቻለሁ።” ቅርጫቱንም በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት አስቀምጠው፤ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ስገድ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆም፥ ጌታ ሆይ፥ አንተ የሰጠኸኝን የምድሪቱን ፍሬ በኵራት አቅርቤአለሁ።’ አንተም በአምላክህ በጌታ ፊት አኑረው፥ በአምላክህም በጌታ ፊት ስገድ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም እነሆ፥ አቤቱ፥ አንተ የሰጠኸኝን ማርና ወተት የምታፈስሰውን የምድሪቱን ፍሬ ቀዳምያት አቅርቤአለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁንም እነሆ፥ አቤቱ፥ አንተ የሰጠኸኝን የምድሪቱን ፍሬ በኩራት አቅርቤአለሁ። አንተም በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት አኑረው፥ በአምላክህም በእግዚአብሔር ፊት ስገድ። |
“ይህን ስጦታ በፈቃደኛነት መስጠት እንችል ዘንድ እኔ ማነኝ? ሕዝቤስ ማነው? ሁሉ ነገር ከአንተ የተቀበልነው ስጦታ ነው፤ እነሆ የአንተ የነበረውንም መልሰን ሰጥተንሃል፤
“በየዓመቱ ከምታመርቱት ምርት መጀመሪያ የደረሰውን በኲራት ወደ እኔ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ቤት አምጡ። “የበግን ወይም የፍየልን ግልገል በእናቱ ወተት አትቀቅል።
ከወር መባቻ እስከ ሌላ የወር መባቻ በዓልና ከሰንበት እስከሚቀጥለው ሰንበት ሕዝብ ሁሉ በአዲሲቱ ኢየሩሳሌም ሊሰግዱልኝ ይመጣሉ”፤ ይህን የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።
በሌላው ሰው ላይ የምትፈርድ አንተ ለራስህ የምታመካኘው የለህም፤ በሌላው ሰው ላይ ስትፈርድ በራስህ ላይ ትፈርዳለህ፤ አንተ በሰው ላይ እየፈረድክ፥ ያ የፈረድክበት ሰው የሚያደርገውን ታደርጋለህ።
እግዚአብሔር አምላክህ መሆኑንና በሕጉም የምትመራ መሆንህን ዛሬ አንተ አረጋግጠሃል፤ ሥርዓቱን፥ ትእዛዞቹንና ሕጎቹን ለመጠበቅና ታዛዥ ለመሆን ቃል ገብተሃል፤
ባለጸጋ እንድትሆን ኀይልና ብርታት የሰጠህ እግዚአብሔር አምላክህ መሆኑን አስታውስ፤ እርሱ ይህን የሚያደርግበት ምክንያት ዛሬ እንደሚያደርገው ሁሉ ከቀድሞ አባቶችህ ጋር በመሐላ የገባውን ቃል ኪዳን ያጸና ዘንድ ነው።
መልአኩ ግን “ተው ይህን አታድርግ! እኔ ከአንተና ከወንድሞችህ ከነቢያት ጋር የዚህን መጽሐፍ ቃል ከሚፈጽሙ ሰዎች ጋር አገልጋይ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ!” አለኝ።