ዘዳግም 23:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ዐሞናዊም ሆነ ሞአባዊ ወይም የእነርሱ ዘር የሆነ ሁሉ እስከ ዐሥር ትውልድ እንኳ የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ አባል አይሁን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሞናዊም ሆነ ሞዓባዊ ወይም ማንኛውም የርሱ ዘር፣ እስከ ዐሥር ትውልድ እንኳ ቢሆን ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ አይግባ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አሞናዊም ሆነ ሞዓባዊ ወይም ማናቸውም የእርሱ ዘር፥ እስከ ዐሥር ትውልድ እንኳን ቢሆን ወደ ጌታ ጉባኤ አይግባ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አሞናዊ ወይም ሞዓባዊ ወደ እግዚአብሔር ቤት አይግባ፤ እስከ ዐሥር ትውልድ ድረስ ለዘለዓለም ወደ እግዚአብሔር ቤት አይግባ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከግብፅ በወጣችሁ ጊዜ እንጀራና ውኃ ይዘው በመንገድ ላይ አልተቀበሉአችሁምና፥ በመስጴጦምያ ካለው ከፋቱራ የቢዖርን ልጅ በለዓምን ዋጋ ሰጥተው ይረግምህ ዘንድ አምጥተውብሃልና አሞራዊና ሞዓባዊ ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ አይግባ፤ እስከ አሥር ትውልድ ድረስ ለዘላለም ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ አይግባ። |
በአጠገቡም ቆሞ የነበረው ጦቢያ በበኩሉ፦ “እነርሱ ምን ዐይነት ቅጽር መሥራት ይችላሉ? የእነርሱ ግንብ ቀበሮ እንኳ ብትወጣበት ሊፈርስ ይችላል!” ሲል በማፌዝ ተናገረ።
ሰንባላጥ፥ ጦቢያና የዐረብ፥ የዐሞን፥ የአሽዶድም ሕዝብ ጭምር የኢየሩሳሌምን ቅጽር ግንብ እንደገና መልሰን በመሥራት ረገድ ጥሩ የሥራ ውጤት ማስገኘታችንንና በቅጽሮቹ መካከል የነበሩት ክፍት ቦታዎች መዘጋታቸውን በሰሙ ጊዜ በብርቱ ተቈጡ፤
ወደ እግዚአብሔር የተጠጋ ባዕድ ሰው “እግዚአብሔር ከራሱ ሕዝብ ይለየኛል” ብሎ አያስብ፤ ጃንደረባ የሆነ ሰው ልጅ ባለመውለዱ፦ “እንደ ደረቅ ዛፍ ነኝ” አይበል።
እግዚአብሔር ስለ ዐሞን እንዲህ ይላል፦ “እስራኤል ወንዶች ልጆች የሉትምን? ወራሾች የሉትምን? ታዲያ ሚልኮም የተባለውን ጣዖት የሚያመልኩ ወገኖች የጋድን ነገድ አስለቅቀው በከተሞቹ የሰፈሩት ለምንድን ነው?
የኢየሩሳሌም ሕዝብ ጠላቶች ከፍተኛ ዋጋ ያላቸውን የሕዝቡን ሀብት ዘረፉ፤ ወደ እግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ እንዳይገቡ የተከለከሉ አሕዛብ እንኳ ቤተ መቅደስዋን ሲወሩ ታዩ።
“ከጋብቻ ውጪ ዲቃላ ሆኖ የተወለደና የእርሱም ዘር ሆኖ የተወለደ ሁሉ እስከ ዐሥር ትውልድ እንኳ ወደ እግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ ገብቶ አይቈጠር።