La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘዳግም 23:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“በአንድ ሰው የወይን ተክል መካከል በምታልፍበት ጊዜ ከፍሬው የምትፈልገውን ያኽል ብላ፤ ነገር ግን በማናቸውም ዕቃ ከፍሬው አትውሰድ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ወደ ባልንጀራህ የወይን ተክል ቦታ በምትገባበት ጊዜ፣ ያሠኘህን ያህል መብላት ትችላለህ፤ ነገር ግን አንዳችም በዕቃህ አትያዝ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

“ወደ ባልንጀራህ ወይን ቦታ በገባህ ጊዜ እስክትጠግብ ድረስ ከወይኑ ብላ፥ ወደ ዕቃህ ግን ከእርሱ ምንም አትውሰድ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

“ወደ ባል​ን​ጀ​ራህ እርሻ በገ​ባህ ጊዜ እሸ​ቱን በእ​ጅህ ቀጥ​ፈህ ብላ፤ ወዳ​ል​ታ​ጨ​ደው ወደ ባል​ን​ጀ​ራህ እህል ግን ማጭድ አታ​ግባ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ወደ ባልንጀራህ ወይን ቦታ በገባህ ጊዜ እስክትጠግብ ድረስ ከወይኑ ብላ፤ ወደ ዕቃህ ግን ከእርሱ ምንም አታግባ።

Ver Capítulo



ዘዳግም 23:24
10 Referencias Cruzadas  

የምስጋና መሥዋዕት ለእግዚአብሔር አቅርብ፤ ስእለትህንም ለልዑል ስጥ።


የሚቃጠል መሥዋዕት ይዤ ወደ ቤትህ እገባለሁ፤ ስእለቴንም አቀርብልሃለሁ።


በኋላ እንዳትጸጸት ለእግዚአብሔር ከመሳልህ በፊት ተጠንቅቀህ አስብ።


“ለእስራኤል ሕዝብ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ አንድ ሰው ለእግዚአብሔር ስእለት ተስሎ ሲፈጸምለት፥ ያ የተሳለው ስለት ሰውን ለመስጠት ከሆነ የመዋጀት ዋጋው እንደ ገመትከው ሆኖ እንደሚከተለው ይሁን፦


አማኞች ወንድሞችን በችግራቸው እርዱ፤ በእንግድነት የሚመጡትንም ተቀበሉ።


“ምድርና በእርስዋም ያለው ሁሉ የጌታ ነው።”


ነገር ግን ለአምላክህ ለእግዚአብሔር በፍላጎትህ በተሳልከው መሠረት፥ አፍህ የተናገረውን በጥንቃቄ መፈጸም አለብህ።


በአንድ ሰው የእህል ማሳ ውስጥ በምታልፍበትም ጊዜ እሸቱን በእጅህ እየቈረጥህ መብላት ትችላለህ፤ ነገር ግን ሰብሉን አጭደህ አትውሰድ።


ከገንዘብ ፍቅር ራቁ፤ ያላችሁ ይብቃችሁ፤ እግዚአብሔር “ከቶ አልጥልህም፤ ፈጽሞም አልተውህም” ብሎአል።


የሕዝቡ መሪዎች በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ስም ምለውላቸው ስለ ነበረ እስራኤላውያን እነርሱን አልገደሉአቸውም። ስለዚሁም ጉዳይ እስራኤላውያን ሁሉ በመሪዎቻቸው ላይ አጒረመረሙ፤