ይህም የሆነበት ምክንያት ከሴሎ በመጣው በነቢዩ አኪያ አማካይነት ስለ ናባጥ ልጅ ስለ ኢዮርብዓም እግዚአብሔር የተናገረው ቃል እንዲፈጸም ነው፤ ንጉሥ ሮብዓምም የሕዝቡን ሐሳብ ችላ በማለት ሳይቀበል የቀረበትም ምክንያት እግዚአብሔር ይህን ለውጥ ለማድረግ ስለ ወሰነ ነው።
ዘዳግም 2:30 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ነገር ግን ሲሖን ንጉሥ ሴዎን በእርሱ ግዛት ውስጥ አልፈን እንድንሄድ ባለመፍቀዱ፥ አሁን እንዳደረገው አምላካችሁ እግዚአብሔር በእጃችሁ አሳልፎ ሊሰጠው ስለ ፈቀደ ትዕቢተኛና እልኸኛ አደረገው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሁን እንጂ የሐሴቦን ንጉሥ ሴዎን እንድናልፍ አልፈቀደልንም፤ ምክንያቱም አምላካችሁ እግዚአብሔር አሁን እንዳደረገው ሁሉ እርሱን በእጃችሁ አሳልፎ ለመስጠት መንፈሱን አደንድኖት፣ ልቡንም አጽንቶት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የሐሴቦን ንጉሥ ሴዎን ግን ያሳልፈን ዘንድ አልፈቀደም፥ እንደ ዛሬው ሁሉ በእጅህ አሳልፎ ይሰጠው ዘንድ፥ ጌታ አምላካችሁ መንፈሱን አደንድኖታልና ልቡንም አጽንቶታልና።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሐሴቦን ንጉሥ ሴዎን ግን ያሳልፈን ዘንድ አልፈቀደም፤ እንደ ዛሬው ሁሉ በእጅህ አሳልፎ ይሰጠው ዘንድ አምላክህ እግዚአብሔር መንፈሱን አደንድኖታልና፥ ልቡንም አጽንቶታልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሐሴቦን ንጉሥ ሴዎን ግን ያሳልፈን ዘንድ አልፈቀደም፤ እንደ ዛሬው ሁሉ በእጅህ አሳልፎ ይሰጠው ዘንድ አምላክህ እግዚአብሔር መንፈሱን አደንድኖታልና፥ ልቡንም አጽንቶታልና። |
ይህም የሆነበት ምክንያት ከሴሎ በመጣው በነቢዩ አኪያ አማካይነት ስለ ናባጥ ልጅ ስለ ኢዮርብዓም እግዚአብሔር የተናገረው ቃል እንዲፈጸም ነው፤ ንጉሥ ሮብዓምም የሕዝቡን ሐሳብ ችላ በማለት ሳይቀበል የቀረበትም ምክንያት እግዚአብሔር ይህን ለውጥ ለማድረግ ስለ ወሰነ ነው።
ይህም የሆነበት ምክንያት ከሴሎ በመጣው በነቢዩ አኪያ አማካይነት ስለ ናባጥ ልጅ ስለ ኢዮርብዓም እግዚአብሔር የተናገረው ቃል እንዲፈጸም ነው፤ ንጉሥ ሮብዓምም የሕዝቡን ሐሳብ ችላ በማለት ሳይቀበል የቀረበትም ምክንያት ይኸው ነው።
ሙሴና አሮንም እነዚህን ተአምራት በንጉሡ ፊት አደረጉ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር የንጉሡን ልብ ስላደነደነ እስራኤላውያን ከምድሪቱ እንዲወጡ አልፈቀደላቸውም።
እንደገናም እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “እንግዲህ አሁን ወደ ግብጽ መመለስህ ስለ ሆነ፥ በሰጠሁህ ኀይል የምታደርጋቸውን ተአምራት በፈርዖን ፊት መፈጸም እንዳለብህ አትዘንጋ፤ ሆኖም እኔ የፈርዖንን ልብ ስለማደነድን ሕዝቡን በቀላሉ አይለቅም።
ሲሖን ግን የእስራኤል ሕዝብ በግዛቱ አልፈው እንዲሄዱ አልፈቀደላቸውም፤ እንዲያውም ሠራዊቱን ሁሉ ሰብስቦ በበረሓ ውስጥ ወዳለችው ወደ ያሀጽ በመሄድ በእስራኤላውያን ላይ ጦርነት አደረገ።
ከዚያም በኋላ እስራኤላውያን ተመልሰው ወደ ባሳን የሚወስደውን መንገድ ተከትለው ሄዱ፤ የባሳን ንጉሥ ዖግ በኤድረዒ ከእነርሱ ጋር ጦርነት ለመግጠም ከመላ ሠራዊቱ ጋር ወጣ።
እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ይህን ሰው አትፍራው፤ በእርሱና በሕዝቡ በምድሪቱም ላይ ድል እንድትጐናጸፍ አደርግሃለሁ፤ በሐሴቦን ሆኖ ይገዛ በነበረው በአሞራውያን ንጉሥ በሲሖን ላይ ያደረግኸውን ሁሉ በዚህም ላይ አድርግበት።”
“ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፤ ‘ተመልከት እኔ ንጉሥ ሲሖንንና ምድሩን በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼሃለሁ፤ አሁን ድል በማድረግ ምድሩን ወርሰህ ስፈርበት።’