ሚክያስም “አንተ በደኅና ከተመለስክማ እግዚአብሔር በእኔ አማካይነት አልተናገረም ማለት ነዋ!” አለው፤ ቀጥሎም ድምፁን ከፍ በማድረግ “በዚህ የምትገኙ ሕዝቦች ሁሉ እኔ የተናገርኩትን ሁሉ ልብ ብላችሁ አድምጡ!” አለ።
ዘዳግም 18:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድ ነቢይ በእግዚአብሔር ስም ትንቢት ተናግሮ ቃሉ ሳይፈጸም ቢቀር ያ ትንቢት ነቢዩ በግምት የተናገረው ነው እንጂ ከእግዚአብሔር ተሰጥቶት የተናገረው ቃል ስላልሆነ ልትፈራው አይገባም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነቢዩ በእግዚአብሔር ስም የተናገረው ካልተፈጸመ ወይም እውነት ሆኖ ካልተገኘ፣ መልእክቱ እግዚአብሔር የተናገረው አይደለም። ያ ነቢይ በድፍረት ተናግሮታልና እርሱን አትፍራው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነቢዩ በጌታ ስም የተናገረው ካልተፈጸመ ወይም እውነት ሆኖ ካልተገለጸ፥ መልእክቱ ጌታ የተናገረው አይደለም። ያ ነቢይ በድፍረት ተናግሮታልና እርሱን አትፍራው።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያ ነቢይ በእግዚአብሔር ስም ከተናገረው ሁሉ ቃሉ ባይደርስ፤ እንደ ተናገረውም ባይሆን እግዚአብሔር ያን ቃል አልተናገረውም፤ ነቢዩ በሐሰት ተናግሮታልና አትስማው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነቢዩ በእግዚአብሔር ስም በተናገረ ጊዜ የተናገረው ነገር ባይሆን ባይመጣም፥ ያ ነገር እግዚአብሔር ያልተናገረው ነው፤ ነቢዩ በድፍረቱ ተናግሮታል እርሱን አትፍራው። |
ሚክያስም “አንተ በደኅና ከተመለስክማ እግዚአብሔር በእኔ አማካይነት አልተናገረም ማለት ነዋ!” አለው፤ ቀጥሎም ድምፁን ከፍ በማድረግ “በዚህ የምትገኙ ሕዝቦች ሁሉ እኔ የተናገርኩትን ሁሉ ልብ ብላችሁ አድምጡ!” አለ።
በዚያን ዘመን ንጉሥ ሕዝቅያስ በጠና ታሞ ለመሞት ተቃርቦ ነበር፤ የአሞጽ ልጅ ነቢዩ ኢሳይያስ ሊጐበኘው ሄዶ “እግዚአብሔር ‘ከሕመምህ አትድንም፤ መሞትህም ስለማይቀር ሁሉን ነገር አስተካክል’ ብሎሃል” ሲል ነገረው።
ጣዖቶቻችሁንም አምጡና በሚፈጸምበት ጊዜ እንድናውቀው ወደ ፊት የሚሆነውን ሁሉ እስቲ ይንገሩን፤ ወደፊት ውጤታቸው ምን እንደሚሆን አስተውለን እንረዳ ዘንድ የቀድሞዎቹ ነገሮች ምን እንደ ሆኑ ይንገሩን፤ ወይም ወደፊት ምን እንደሚከሠት ያስረዱን።
እንዲህም ሲል ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፦ “እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ይህን እንደምታደርግ ገና በአገሬ ሳለሁ ተናግሬ አልነበረምን? ከፊትህ ኰብልዬ ወደ ተርሴስ ለመሄድ ያቀድኩትም በዚህ ምክንያት ነበር፤ አንተ ቸርና ይቅር ባይ፥ ታጋሽና ምሕረትህ የበዛ፥ በዘለዓለማዊ ፍቅር የተመላህ፥ ቊጣህን መልሰህ ምሕረት የምታደርግ አምላክ መሆንህን ዐውቅ ነበር።