“በግድያ ወንጀል የተከሰሰ ማንኛውም ሰው የሞት ፍርድ ሊበየንበት የሚችለው ሁለት ወይም ከሁለት በላይ የሆኑ ሰዎች የመሰከሩበት እንደ ሆነ ነው፤ የአንድ ሰው ምስክርነት ግን ለግድያ ወንጀል የተከሰሰውን ሰው ሊያስጠይቀው አይችልም።
ዘዳግም 17:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሆኖም በዚህ ሁኔታ በሞት መቀጣት የሚገባው ሁለት ወይም ሦስት ሰዎች በእርሱ ላይ ከመሰከሩበት በኋላ ነው፤ ምስክሩ አንድ ብቻ ከሆነ ግን ያ ሰው አይገደል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሞት የሚገባው ሰው፣ በሁለት ወይም በሦስት ሰዎች ምስክርነት ይገደል፤ ነገር ግን በአንድ ሰው ምስክርነት ብቻ ማንም ሰው አይገደል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሞት የሚገባው ሰው፥ በሁለት ወይም በሦስት ሰዎች ምስክርነት ይገደል፤ ነገር ግን በአንድ ሰው ምስክርነት ብቻ ማንም ሰው አይገደል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሁለት ወይም በሦስት ምስክሮች ሞት የሚገባቸው ይገደሉ፤ በአንድ ምስክር ግን አይገደሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሁለት ወይም በሦስት ምስክሮች አፍ ሞት የሚገባው ይገደል፤ በአንድ ምስክር አፍ አይገደል። |
“በግድያ ወንጀል የተከሰሰ ማንኛውም ሰው የሞት ፍርድ ሊበየንበት የሚችለው ሁለት ወይም ከሁለት በላይ የሆኑ ሰዎች የመሰከሩበት እንደ ሆነ ነው፤ የአንድ ሰው ምስክርነት ግን ለግድያ ወንጀል የተከሰሰውን ሰው ሊያስጠይቀው አይችልም።
“የአንድን ሰው ወንጀለኛነት ለማረጋገጥ አንድ ምስክር ብቻ አይበቃም፤ አንድ ሰው ወንጀለኛ መሆኑን ለማረጋገጥ ሁለት ወይም ሦስት ምስክሮች ያስፈልጋሉ።