ዘዳግም 17:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያን በኋላ ሰው ሁሉ ይህን ሰምቶ ይፈራል፤ ይህንንም የመሰለ ክፉ ነገር ለመፈጸም የሚዳፈር አይኖርም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕዝቡም ሁሉ ይህን ሲሰማ ይፈራል፤ ከዚያ ወዲያም እንዲህ ያለውን የንቀት ድርጊት አይደግመውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕዝቡም ሁሉ ሰምቶ ይፈራል፥ ከዚያም ወዲያ አይዳፈርም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕዝቡም ሁሉ ሰምቶ ይፈራል፤ ከዚያም ወዲያ ደግሞ አይበድልም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕዝቡም ሁሉ ሰምቶ ይፈራል፥ ከዚያም ወዲያ አይኮራም። |
“እግዚአብሔር አምላክህ እንድትኖርባቸው ከሰጠህ ከተሞች በአንደኛዋ ውስጥ አንዳንድ ወራዶች ሰዎች ከመካከልህ ተነሥተው ነዋሪዎቹን ወደማታውቃቸው ወደ ሌሎች አማልክት ‘እንሂድና እናምልክ’ ብለው ወደ ጥፋት መንገድ መርተው መውሰዳቸውን ትሰማ ይሆናል፤
ዳኛውን ወይም አምላክህን እግዚአብሔርን በማገልገል ላይ ያለውን ካህን ባለመታዘዝ የሚዳፈር ሰው ቢኖር በሞት ይቀጣ። በዚህም ዐይነት እንደዚህ ያለውን ክፉ ነገር ሁሉ ከእስራኤል ታስወግዳለህ።