ዘዳግም 13:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዚያችን ከተማ ሰዎች ሀብት በሙሉ ሰብስበህ በማምጣት በከተማይቱ አደባባይ እንዲከመር አድርግ፤ ከዚያም በኋላ ከተማይቱንና ሀብቱን ሁሉ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አድርገህ በእሳት አቃጥለው፤ ዳግመኛም እንዳትሠራ ለዘለዓለም ፍርስራሽ ሆና ትቅር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በከተማዪቱ የተገኘውን የምርኮ ዕቃ ሁሉ በአደባባይዋ መካከል ላይ ሰብስበህ፣ ከተማዪቱን ከነምርኮዋ እንዳለ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር የሚቀርብ መሥዋዕት አድርገህ በሙሉ አቃጥል። ለዘላለም እንደ ፈረሰች ትቅር፤ ተመልሳም አትሠራ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በከተማዪቱ የተገኘውን የምርኮ ዕቃ ሁሉ በአደባባይዋ መካከል ላይ ሰብስበህ፥ ከተማዪቱን ከነምርኮዋ ለጌታ ለእግዚአብሔር የሚቀርብ መሥዋዕት አድርገህ በሙሉ አቃጥል። ለዘለዓለም እንደ ፈረሰች ትቅር፤ ተመልሳም አትሠራ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዕቃዋንም ሁሉ ወደ አደባባይዋ ትሰበስባለህ፤ ከተማይቱንም፥ ዕቃዋንም ሁሉ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት በእሳት ፈጽመህ ታቃጥላለህ፤ ለዘለዓለምም ወና ትሆናለች፤ ደግሞም አትሠራም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዕቃዋንም ሁሉ ወደ አደባባይዋ ትሰበስባለህ፥ ከተማይቱንም ዕቃዋንም ሁሉ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር በእሳት ፈጽመህ ታቃጥላለህ፤ ለዘላለምም ወና ትሆናለች፥ ደግሞም አትሠራም። |
ከተሞች ፈርሰው ባድማ እንዲሆኑ አድርገሃል፤ ምሽጎቻቸውንም አፈራርሰሃል፤ ጠላቶቻችን የሠሩአቸው ቤተ መንግሥቶች እንዳልነበሩ ሆነዋል፤ እስከ ዘለዓለምም እንደገና አይሠሩም።
ስለዚህ የአሞን ከተማ በሆነችው በራባ ላይ የጦርነት ክተት ጥሪ ድምፅ የማሰማበት ጊዜ ይመጣል፤ እርስዋ፥ በፍርስራሽ ክምር የተሞላች ባድማ ትሆናለች፤ መንደሮችዋም በእሳት ይቃጠላሉ፤ ከዚህ በኋላ እስራኤላውያን አስቀድመው እነርሱን የበዘበዙአቸውን መልሰው ይበዘብዛሉ።
ዓሣ አጥማጆች መረባቸውን የሚያሰጡበት አለት ብቻ አግጥጦ ይቀራል፤ ከተማይቱ ዳግመኛ አትታደስም፤ ይህም የሚሆነው እኔ ልዑል እግዚአብሔር ስለ ተናገርኩ ነው።”
ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል “ሰማርያን በሜዳ ላይ እንደሚታይ የቤት ፍርስራሽ ክምር አደርጋለሁ፤ የወይን መትከያ ቦታ ትሆናለች፤ የከተማይቱንም ፍርስራሽ ድንጋይ ወደ ሸለቆ አፈሰዋለሁ፤ መሠረቶችዋንም እገልጣለሁ።
ጣዖቶቻቸውን በእሳት አቃጥል፤ በእነርሱ ላይ የተለበጠውን ብር ወይም ወርቅ የራስህ ንብረት አድርገህ ለመውሰድ ልብህ አይመኝ፤ ይህን ብታደርግ ወጥመድ ይሆንብሃል፤ እግዚአብሔርም አምልኮ ጣዖትን ስለሚጠላ ብርቱ ጥፋትን ያስከትልብሃል።
እነዚህንም የረከሱ ጣዖቶች ወደ ቤትህ አታስገባ፤ ብታስገባ ግን አንተም እንደ እነርሱ ትጠፋለህ፤ እነርሱ ለጥፋት የተገቡ ስለ ሆነ በጣም ልትጠላቸውና ልትጸየፋቸው ይገባል።
ከዚህ በኋላ በእግዚአብሔር ዕቃ ግምጃ ቤት ካስቀመጡአቸው ከብሩና ከወርቁ እንዲሁም በነሐስና በብረት ከተሠሩት ዕቃዎች በቀር ከተማይቱንና በእርስዋ ያሉትን ነገሮች ሁሉ አቃጠሉ።
በዚያን ጊዜ ኢያሱ፦ “ይህቺን የኢያሪኮን ከተማ ለመገንባት የሚነሣ የተረገመ ይሁን፤ መሠረቱን ሲጥል የበኲር ልጁ ይጥፋ፤ መዝጊያውን ሲያቆም የመጨረሻ ልጁ ይጥፋ፤” ብሎ ረገመ።