ዘዳግም 1:34 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እግዚአብሔርም የማጒረምረም ጩኸታችሁን ሰምቶ ተቈጣ፤ ስለዚህም እንዲህ ሲል ማለ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም እናንተ ያላችሁትን በሰማ ጊዜ ተቈጣ፤ ማለም፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ጌታም የቃላችሁን ድምፅ ሰምቶ ተቆጣም፤ እንዲህም ሲል ማለ፦ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እግዚአብሔርም የቃላችሁን ድምፅ ሰምቶ ተቈጣ፤ እንዲህም ብሎ ማለ፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም የቃላችሁን ድምፅ ሰምቶ ተቆጣ፦ |
ከዚህም በላይ ከዓለም ምድር ሁሉ ውብ የሆነችውንና በማርና በወተት የበለጸገችውን ምድር እሰጣችኋለሁ ብዬ ቃል ገብቼላቸው ነበር። ከዚያ በኋላ ግን በበረሓ እያሉ ወደዚያ እንደማላስገባቸው አረጋግጬ ነገርኳቸው።
አሁን ደግሞ እናንተ በአባቶቻችሁ ስፍራ ተተክታችኋል፤ የእግዚአብሔርንም ቊጣ በእስራኤል ላይ ለማምጣት የተዘጋጀ አዲስ ኃጢአተኛ ትውልድ ሆናችኋል።