እርሱም ለአንተ ታማኝ እንደ ሆነ ተመልክተህ፥ ከእርሱ ጋር ቃል ኪዳንን አደረግህ፤ ከነዓናውያን፥ ሒታውያን፥ አሞራውያን፥ ፈሪዛውያን፥ ኢያቡሳውያንና ጌርጌሳውያን የሚኖሩባትንም የከነዓንን ምድር ለዘሮቹ መኖሪያ ርስት አድርገህ ልትሰጠው ቃል ገባህለት፤ አንተ ታማኝ ስለ ሆንክ ቃል ኪዳንህን አጽንተህ ጠብቀሃል።
ዳንኤል 9:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጌታ ሆይ! ስለ ፈጸምካቸው የጽድቅ ሥራዎች ሁሉ ብለህ ከተቀደሰችው ተራራህ ከኢየሩሳሌም ቊጣህንና መዓትህን እንድታነሣ እንለምንሃለን፤ በኃጢአታችንና በአባቶቻችንም በደል ምክንያት ኢየሩሳሌምና ሕዝብህ በጐረቤቶቻችን ሁሉ መካከል ተዋርደዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጌታ ሆይ፤ ቀድሞ እንዳደረግኸው የጽድቅ ሥራህ ሁሉ፣ ከከተማህ ከኢየሩሳሌም፣ ከቅዱሱም ተራራህ ቍጣህን መልስ፤ በእኛ ኀጢአትና በአባቶቻችን በደል ምክንያት ኢየሩሳሌምና ሕዝብህ በዙሪያችን ባሉት ዘንድ መሣለቂያ ሆነዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጌታ ሆይ፥ ስለ ኃጢአታችንና ስለ አባቶቻችን በደል ኢየሩሳሌምና ሕዝብህ በዙሪያችን ላሉት ሁሉ መሰደቢያ ሆነዋልና እንደ ጽድቅህ ሁሉ ቍጣህና መዓትህ ከከተማህ ከኢየሩሳሌም ከቅዱስ ተራራህ እንዲመለስ እለምንሃለሁ። |
እርሱም ለአንተ ታማኝ እንደ ሆነ ተመልክተህ፥ ከእርሱ ጋር ቃል ኪዳንን አደረግህ፤ ከነዓናውያን፥ ሒታውያን፥ አሞራውያን፥ ፈሪዛውያን፥ ኢያቡሳውያንና ጌርጌሳውያን የሚኖሩባትንም የከነዓንን ምድር ለዘሮቹ መኖሪያ ርስት አድርገህ ልትሰጠው ቃል ገባህለት፤ አንተ ታማኝ ስለ ሆንክ ቃል ኪዳንህን አጽንተህ ጠብቀሃል።
እኔ እግዚአብሔር አምላክህ እጅግ ቀናተኛ ስለ ሆንኩ ተቀርጾ የተሠራውን ማንኛውም ጣዖት አታምልክ፤ አትስገድለትም፤ እኔ የሚጠሉኝን ሁሉ እቀጣለሁ፤ ዘራቸውንም ሁሉ እስከ ሦስትና አራት ትውልድ ድረስ እበቀላለሁ።
እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ በጣም ተቈጥቶአል፤ በኀያልነቱም ይቀጣቸዋል፤ ተራራዎች ይናወጣሉ፤ የሞቱ ሰዎችም አስከሬን እንደ ጥራጊ በየመንገዱ ዳር ይወድቃል፤ ይህም ሁሉ ሆኖ የእግዚአብሔር ቊጣ አይበርድም፤ እንደገናም ሊቀጣቸው ተዘጋጅቶአል።
በስደት እንዲበታተኑ ባደረግሁባቸው በምድር መንግሥታት ሁሉ ዘንድ የተጠሉ፥ የተሰደቡ፥ የመነጋገሪያ ርእስ የሆኑ፥ መሳለቂያና የተወገዙ እንዲሆኑ አደርጋቸዋለሁ።
በጦርነት፥ በራብና በቸነፈር አባርራቸዋለሁ፤ የዓለም ሕዝብ ሁሉ በእነርሱ ላይ ስለሚያዩት ነገር ይደነግጣሉ፤ እንዲበተኑ በማደርግበት ስፍራ ሁሉ በእነርሱ ላይ የማደርሰውን ነገር የሚያዩ ሕዝቦች ሁሉ በመደንገጥ ይሸበራሉ። ሕዝብም ሁሉ መሳቂያና መሳለቂያ ያደርጋቸዋል።
የእስራኤልና የይሁዳ ሕዝብ፥ የእነርሱ ነገሥታት፥ ባለሥልጣኖቻቸው፥ የእነርሱ ካህናትና ነቢያት በሚያደርጉአቸው ክፉ ነገሮች ሁሉ ቊጣዬን አነሣሥተዋል።
በፈጸምሽው ግድያ በደለኛ ሆነሻል፤ በሠራሻቸውም ጣዖቶች ረክሰሻል፤ ስለዚህ የምትጠፊበት ጊዜ ቀርቦአል! ያፋጠንሽውም አንቺ ነሽ። ሕዝቦች እንዲቀልዱብሽ፥ አገሮችም በንቀት አመለካከት እንዲያፌዙብሽ ያደረግኹትም ስለዚህ ነው።
በባሕሩና ቤተ መቅደሱ በተሠራበት ውብ ኮረብታ መካከል ባለው ስፍራ ታላላቅ ንጉሣዊ ድንኳኖችን ይተክላል፤ ይህም ሁሉ ሆኖ በመጨረሻው ራሱ ይጠፋል፤ የሚረዳውም አያገኝም።”
“እስራኤል ሆይ! በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደ ሆንኩ ታውቃላችሁ፤ በተቀደሰው ተራራዬ በጽዮን ላይ እኖራለሁ፤ ኢየሩሳሌምም የተቀደሰች ከተማ ትሆናለች፤ ከእንግዲህ ወዲህ የባዕድ ወታደሮች አይወሩአትም።
እኔ እንድኖርባት ወደ ተቀደሰችው ከተማዬ ወደ ኢየሩሳሌም እመለሳለሁ፤ የታመነች ከተማ በመሆን ትታወቃለች፤ እኔ የሠራዊት አምላክ የምኖርበት ተራራ፥ የተቀደሰ ተራራ ተብሎ ይጠራል፤