ዳንኤል 8:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በክፋት ምክንያት ሠራዊቱና መደበኛው የሚቃጠል መሥዋዕት ለእርሱ ተሰጠ፤ እርሱም እውነትን ወደ መሬት ጣለ፤ የሚያደርገውም ነገር ሁሉ እየተሳካለት ሄደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዐመፅ የተነሣም የቅዱሳን ሰራዊት ከዘወትሩ መሥዋዕት ጋራ ለርሱ ዐልፎ ተሰጠ፤ የሚያደርገው ሁሉ ተከናወነለት፤ እውነትም ወደ ምድር ተጣለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሠራዊቱም ከኃጢአት የተነሣ ከዘወትሩ መሥዋዕት ጋር ተሰጠው፥ እርሱም እውነትን ወደ ምድሩ ጣለ፥ አደረገም ተከናወነም። |
እግዚአብሔር ሆይ! ከአንተ ጋር በምከራከርበት ጊዜ ሁሉ አንተ ትክክለኛ ነህ፤ አሁን ግን ስለ ትክክለኛ ፍርድ ጥያቄ አለኝ፤ የኃጢአተኛ ሕይወት የተቃና የሚሆንበት ምክንያት ምንድን ነው? አታላዮችስ ሁሉ ነገር የሚሳካላቸው ስለምንድን ነው?
የሶርያ ንጉሥ የማረከውን ሀብት ሁሉ ይዞ ይመለሳል፤ ልቡ ግን የተቀደሰውን ቃል ኪዳን ለማጥፋት ነው፤ የፈለገውን ሁሉ ካደረገ በኋላ ወደ አገሩ ይሄዳል።
ያም በግ በቀንዶቹ ለመጐሸም ወደ ምዕራብ፥ ወደ ሰሜን፥ ወደ ደቡብ ሲቃጣ አየሁ፤ በፊቱ ቀርቦ የሚቋቋመው ወይም ከኀይሉ ማምለጥ የሚችል አውሬ አልነበረም፤ የፈለገውን ሁሉ ያደርግ ነበር፤ ይበልጥም እየበረታ ሄደ።
ቅዱሳንን እንዲዋጋና ድል እንዲነሣቸው ሥልጣን ተሰጠው፤ በነገድና በወገን፥ በልዩ ልዩ ቋንቋዎች በሚናገሩና በሕዝብ ሁሉ ላይ ሥልጣን ተሰጠው።