ዳንኤል 7:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን የልዑል እግዚአብሔር ቅዱሳን መንግሥቱን ወርሰው ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም የራሳቸው እንዲሆን ያደርጉታል።’ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን የልዑሉ ቅዱሳን መንግሥቱን ይወስዳሉ፤ ለዘላለምም ይይዙታል፤ አዎን፤ ለዘላለም ይይዙታል።’ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን የልዑሉ ቅዱሳን መንግሥቱን ይወስዳሉ፥ እስከ ዘላለም ዓለምም መንግሥቱን ይወርሳሉ። |
እነዚህ እንደ በጎች እንዲሞቱና እንዲቀበሩ ይደረጋሉ፤ እረኛ በጎችን እንደሚመራ ሞትም እነዚህን ወደ መቃብር ይመራል፤ ትክክለኞች ሰዎች በማለዳ በመቃብራቸው ላይ ይመላለሳሉ፤ ሥጋቸውም በመቃብር ውስጥ ይበሰብሳል፤ የሙታን ዓለምም መኖሪያቸው ይሆናል። ደጋግ ሰዎችም በማለዳ ተነሥተው በእነርሱ ላይ ሥልጣናቸውን ያሳያሉ።
የብዙ አሕዛብ መንግሥታት የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔር ወደ ሰጣቸው አገር እንዲመለሱ ይረዱአቸዋል፤ አሕዛብ እንደ ባሪያዎች ሆነው የእስራኤልን ሕዝብ ያገለግላሉ፤ ቀድሞ እስራኤልን ማርከው የነበሩ አሁን ደግሞ በእስራኤል እጅ ይማረካሉ፤ ስለዚህም የእስራኤል ሕዝብ ቀድሞ ይጨቊኑአቸው የነበሩትን ሁሉ የመግዛት ሥልጣን ይኖራቸዋል።
በልዩ ልዩ አገር የሚኖሩ ሕዝቦችና ልዩ ልዩ ቋንቋ የሚናገሩ ነገዶች ያገለግሉት ዘንድ ሥልጣን፥ ክብርና ንጉሥነት ተሰጠው፤ ግዛቱም የማይጠፋ ዘለዓለማዊ ነው፤ ለመንግሥቱም ፍጻሜ የለውም።
ይህም የሆነው ዘለዓለማዊው መጥቶ ለልዑል እግዚአብሔር ቅዱሳን ፍትሕ እስከ ሰጠበት ጊዜ ድረስ ነው፤ ቅዱሳኑም መንግሥቱን የሚወርሱበት ጊዜ ደረሰ።
በልዑል እግዚአብሔር ላይ በመታበይ ይናገራል፤ የልዑል እግዚአብሔርንም ቅዱሳን ያስጨንቃል፤ የተቀደሱ በዓላትንና ሕጉን ለመለወጥ ያቅዳል፤ ቅዱሳኑም ለሦስት ዓመት ተኩል በእርሱ ሥልጣን ሥር ይሆናሉ።
ከሰማይ ሁሉ በታች በምድር ላይ ያለ የመንግሥት ሥልጣን፥ ኀይልና ገናናነት ሁሉ ለልዑል እግዚአብሔር ቅዱሳን ይሰጣል፤ መንግሥታዊ ሥልጣናቸውም ለዘለዓለም ጸንቶ ይኖራል፤ የዓለም ግዛቶች ሁሉም ለእነርሱ በመታዘዝ ያገለግሉአቸዋል።’ ”
“በጽዮን ተራራ ከጥፋት የሚያመልጡ ይገኛሉ፤ የጽዮን ተራራም የተቀደሰች ትሆናለች፤ የያዕቆብም ሕዝብ ተወስዶባቸው የነበረውን ንብረት መልሰው ይወስዳሉ።
የእግዚአብሔር ሰዎች በዓለም ላይ እንደሚፈርዱ አታውቁምን? ታዲያ፥ በዓለም ላይ የምትፈርዱ ሲሆን በዚህ በትንሽ ነገር ላይ መፍረድ ያቅታችኋልን?
የእኛ ውጊያ ከሰዎች ጋር ሳይሆን በዚህ በጨለማ ዘመን ከሚሠሩት ገዢዎች፥ ከባለ ሥልጣኖችና ከዚህ ዓለም ኀይሎችና ይህም ማለት በሰማይ ካሉት ከርኩሳን መናፍስት ሠራዊት ጋር ነው።
ከዚህ በኋላ ዙፋኖችን አየሁ፤ በዙፋኖቹም ላይ የመፍረድ ሥልጣን የተሰጣቸው ተቀምጠው አየሁ፤ ስለ ኢየሱስ በመመስከራቸውና ስለ እግዚአብሔር ቃል ራሶቻቸው የተቈረጡባቸውን ሰዎች ነፍሶች አየሁ፤ እነርሱ ለአውሬውና ለምስሉ ያልሰገዱ፥ ምልክቱንም በግንባራቸውም ሆነ በእጃቸው ላይ ያላደረጉ ናቸው፤ እነርሱ ከሞት ተነሥተው ከክርስቶስ ጋር ሺህ ዓመት ነገሡ።
ከእንግዲህ ወዲህ ሌሊት አይኖርም፤ ጌታ አምላክ ስለሚያበራላቸው የመብራት ወይም የፀሐይ ብርሃን አያስፈልጋቸውም፤ ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ይነግሣሉ።